የኢትዮጵያ የመገናኛ ብዙኃን ባለስልጣን ማስጠንቀቂያ
ረቡዕ፣ ግንቦት 11 2013ማስታወቂያ
በዩትዩብ መረጃ የሚያሰራጩ ተቋማት እና ግለሰቦች በአንድ ሳምንት ጊዜ ውስጥ እንዲመዘገቡ የኢትዮጵያ የመገናኛ ብዙኃን ባለስልጣን አሳሰበ። ባለስልጣኑ ዛሬ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የ9 ወራት የስራ አፈጻጸሙን ባስገመገመበት ወቅት እንዳለው በህጋዊ መንገድ ተመዝግበው በማይሰሩ ተቋማትም ሆነ ግለሰቦች ላይ እርምጃ እወስዳለሁ ብሏል። በምክር ቤቱ የሕግ ፍትህ እና ዴሞክራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ጋር በተደረገው ውይይት ባለስልጣኑ በፋይናንስ ኃብት አጠቃቀሙ ተገምግሟል።
ዮሐንስ ገብረእግዚአብሔር
ታምራት ዲንሳ
ነጋሽ መሐመድ