1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚንሥትር ጋዜጣዊ መግለጫ

ማክሰኞ፣ ታኅሣሥ 6 2013

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ስለ ወቅታዊ ጉዳዮች ዛሬ በጽሕፈት ቤቱ መግለጫ ሰጥታል። ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን በትግራይ ክልል ስለሚደረገው ሰብዓዊ ድጋፍና፣ ወደ ሱዳን የሸሹ ኢትዮጵያዊያንን እንዴት መመለስ እንደሚቻል ከተባበሩት መንግሥታት ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ጋር ዛሬ በአዲስ አበባ መነጋገራቸውም ተገልጧል።

https://p.dw.com/p/3mky4
Äthiopien Dina Mufti
ምስል Solomon Muchie/DW

በወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ መግለጫ

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ስለ ወቅታዊ ጉዳዮች ዛሬ በጽሕፈት ቤቱ መግለጫ ሰጥታል። ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን በትግራይ ክልል ስለሚደረገው ሰብዓዊ ድጋፍና፣ ወደ ሱዳን የሸሹ ኢትዮጵያዊያንን እንዴት መመለስ እንደሚቻል ከተባበሩት መንግሥታት ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ጋር ዛሬ ጥዋት በአዲስ አበባ መነጋገራቸውም ተገልጧል። በትናንትናው እለት ብቻ 27 ከባድ የጭነት ተሽከርካሪዎች የምግብ እና የመድኃኒት ቊሳቊሶችን ጭነው ወደ ትግራይ ክልል በማቅናት የርዳታ ሥራው መቀጠሉንም የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት ገልጧል። ትግራይ ክልል ውስጥ ኤርትራዊያን ስደተኞች ከተጠለሉባቸው አራት ካምፖች መካከል የሁለቱ መጠለያ ስደተኞች የነበረውን ጦርነት ሸሽተው ወደ መሃል ሀገር ስለ መምጣታቸውም የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ተናግሯል። የሱዳኑ ጠቅላይ ሚንሥትር ለሁለት ቀናት የሥራ ጉብኝት ወደ ኢትዮጵያ አቅንተው በግማሽ ቀን ስለመመለሳቸውም ማብራሪያ ተሰጥቷል። 
ሰለሞን ሙጬ
ማንተጋፍቶት ስለሺ
እሸቴ በቀለ