1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መግለጫ

ዓርብ፣ ነሐሴ 15 2012

የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በመላው አለም የሚገኙ የኢትዮጵያ አምባሳደሮች ከቀጣዩ ሰኞ ጀምሮ አመታዊ ስብሰባቸውን በአዲስ አበባ እንደሚካሄድ አመለከተ። የሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ ቃል አቀባይ በዛሬው ዕለት በሰጠው መግለጫ የተለያዩ ጉዳዮችንም አንስቷል።።

https://p.dw.com/p/3hJ0b
Dina Mufti Sprecher Außenminister Äthiopien
ምስል Getachew Tedla

«የአምባሳደሮች ስብሰባ ከሰኞ ጀምሮ ይካሄዳል»

በመላው ዓለም የሚገኙ የኢትዮጵያ አምባሳደሮች ከቀጣዩ ሰኞ ጀምሮ አመታዊ ስብሰባቸውን በአዲስ አበባ ያደርጋሉ ተባለ። የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ዛሬ በሰጠው መግለጫ በታላቁ ህዳሴ ግድብ በሶስቱ ሀገራት የተጀመረ ድርድር መቀጠሉንና ኢትዮጵያም በሙሉ ልብ እየተደራደረች መሆኑ ተገልጿል። ከዚህም ሌላ በተለያዩ የአረብ ሃገራት በችግር ላይ የሚገኙ ዜጎችን ወደ ኢትዮጵያ እየተደረገ ስላለው ጥረትም ተጠቅሷል። መግለጫውን የአዲስ አበባው ዘጋቢያችን ሰሎሞን ሙጬ ተከታትሎት ተከታዩን ልኮልናል።

ሰሎሞን ሙጬ

ሸዋዬ ለገሠ

ኂሩት መለሰ