1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኢትዮጵያ ወቅታዊ ኹኔታ እና ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ

ሐሙስ፣ ኅዳር 17 2013

ባለፈው ሳምንት በተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት በከፍተኛ የልዑካን ቡድን አባላት የተደረጉት የሥራ ጉብኝቶች ሀገራቱ ጉዳዩ የኢትዮጵያ የውስጥ ጉዳይ መሆኑን ያረጋገጡበት ነው ሲሉ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ለዶይቼ ቬለ ገልፀዋል።

https://p.dw.com/p/3lsDt
Dina Mufti Sprecher Außenminister Äthiopien
ምስል Getachew Tedla

የኢትዮጵያ ወቅታዊ ኹኔታ እና ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ

ኢትዮጵያ በትግራይ ክልል እየተከናወነ ያለውን ሕግ የማስከበር ተግባር ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብ በማስገንዘብ ረገድ ስኬታማ ሥራ ማከናወኗን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ገለፀ።
ባለፈው ሳምንት በተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት በከፍተኛ የልዑካን ቡድን አባላት የተደረጉት የሥራ ጉብኝቶች ሀገራቱ ጉዳዩ የኢትዮጵያ የውስጥ ጉዳይ መሆኑን ያረጋገጡበት ነው ሲሉ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ለዶይቼ ቬለ ገልፀዋል። የተባበሩት መንግሥታት የፀጥታው ምክር ቤት በዚህ ጉዳይ ላይ ውይይት እንዲያደርግ ጭምር የተገፋው አጀንዳ አለመሳካት ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ይህን ጉዳይ ለመረዳቱ ማሳያ መሆኑንም አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ተናግረዋል።

ሰለሞን ሙጬ

እሸቴ በቀለ


ማንተጋፍቶት ስለሺ