1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኢትዮጵያ ወቅታዊ ሁኔታ በፖለቲካ ምሁር እይታ 

እሑድ፣ ኅዳር 6 2013

በኢትዮጵያ የሽብር ጥቃት ሊፈጽሙ እንደነበር ተደርሶባቸው በቁጥጥር ሥር ዋሉ የተባሉት የአልሸባብና የአይ ኤስ የሽብር ቡድን አባላት አሁን ኢትዮጵያን ኢላማ ያደረጉት ስለ ኢትዮጵያ የውስጥ ጉዳይ የተሳሳተ ግንዛቤ በመያዛቸው መሆኑን አንድ የዲፕሎማሲ እና ዓለም አቀፍ ግንኙነት መምህር ለዶቼ ቬለ ተናገሩ።

https://p.dw.com/p/3lKdw
Äthiopien Konflikt Tigray | Milizen der Amhara-Region
ምስል Tiksa Negeri/REUTERS

በቁጥጥር ሥር ዋሉ የተባሉት የአልሸባብና የአይ ኤስ የሽብር ቡድን አባላት

በኢትዮጵያ የሽብር ጥቃት ሊፈጽሙ እንደነበር ተደርሶባቸው በቁጥጥር ሥር ዋሉ የተባሉት የአልሸባብና የአይ ኤስ የሽብር ቡድን አባላት አሁን ኢትዮጵያን ኢላማ ያደረጉት ስለ ኢትዮጵያ የውስጥ ጉዳይ የተሳሳተ ግንዛቤ በመያዛቸው መሆኑን አንድ የዲፕሎማሲ እና ዓለም አቀፍ ግንኙነት መምህር ለዶቼ ቬለ ተናገሩ። ኢትዮጵያ ያለችበትን ወቅታዊ ሁኔታ በተለይ የአልቃይዳ የምስራቅ አፍሪቃ ክንፍ የሆነው አልሸባብ ለማንሰራራት ምቹ ሁኔታ አድርጎ ገምቶ ይሆናል ያሉት መምህሩ ይህ ግምቱ ስህተት ነው ብለዋል። በሌላ በኩል ትናንት ከሕወሓት ወደ አስመራ ከተማ ተሰነዘረ የተባለው የሮኬት ጥቃት የአፍሪካ ቀንድ ቀጣናን ለመረበሽ ከመነጬ ፍላጎት የተነሳ እንደሆነና ኤርትራ ለደረሰባት ጥቃት ምንም የአፀፋ ምላሽ አለማድረጓ የሁለቱን ሀገራት የዲፕሎማሲ ግንኙነት መጠናከር ማሳያ ነው ብለዋል።

ሰለሞን ሙጬ 
አዜብ ታደሰ