1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤ/ክርስትያን ጥሪ 

ዓርብ፣ ጥቅምት 14 2012

የቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ ባስተላለፈው የሰላም ጥሪ በሃገሪቱ በተለያዩ አካባቢዎች በልዩ ልዩ ምክንያቶች መጠነ ሰፊ ግጭቶች በመከሰታቸው የሰው ህይወት መጥፋቱን በርካታ ንብረት መውደሙን አስታውሷል።ችግሩ እጅግ አሳሳቢ መሆኑን ገልጾ ሁሉም ኢትዮጵያዊያ በአንድነትና በህብረት ከባድ ጉዳት የሚያስከትለው ያለውን ይህን ችግሩን እንዲያስወግድ ጠይቋል።

https://p.dw.com/p/3Rt1U
Äthiopien | Orthodox Church press briefing
ምስል DW/S. Muchie

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ጸሎትና ምህላ አወጀች

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስትያን ከዛሬ ጥቅምት 13፣ 2012 ዓ.ም ጀምሮ ለ ሶስት ቀናት  የሚዘልቅ የጸሎትና ምህላ መንፈሳዊ አዋጅ አወጀች።ቤተ ክርስትያኗ ያለ ሃገር ሰላምና አንድነት እንዲሁም ፍቅርና እድገት መኖር ስለማይችል መላው ህዝብ እንደየእምነቱና ሃይማኖቱ ስርአት ከዛሬ ጀምሮ ለ ሶስት ቀናት ያህል በጾም ፣በጸሎትና በሃዘን ስለ ሃገር ሰላም በአንድነት ጥሪውን ለፈጣሪውና ለአምላኩ ያደርስ ዘንድ ጥሪ አቅርባለች ። መንፈሳዊ አዋጁንም አውጃለች። የቤተክርስትያኗ ቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ ባስተላለፈው የሰላም ጥሪ በሃገሪቱ በተለያዩ አካባቢዎች በልዩ ልዩ ምክንያቶች ብሄርና ሀይማኖትን እንዲሁም ቋንቋን መሰረት ያደረገ መጠነ ሰፊ ግጭቶች በመከሰታቸው የሰው ህይወት መጥፋቱን በርካታ ንብረት መውደሙን አስታውሷል።ችግሩ እጅግ አሳሳቢ ከመሆኑም በላይ ጊዜ የማይሰጥ መሆኑን ገልጾ ሁሉም ኢትዮጵያዊያ በአንድነትና በህብረት ከባድ ጉዳት የሚያስከትለው ያለውን ይህን ችግሩን እንዲያስወግድ ጠይቋል።መግለጫውን የተከታተለው የአዲስ አበባው ዘጋቢያችን ዝርዝሩን አዘጋጅቷል።


ሰሎሞን ሙጬ 


ኂሩት መለሰ
ተስፋለም ወልደየስ