እርቀ ሰላም በኢ/ኦ/ተ/ቤ
እሑድ፣ ሐምሌ 29 2010ማስታወቂያ
ለረዥም ዓመታት በይፋም ምስጢርም ልዩነቱን አቀራርቦ ሰላም አንድነቷን ለመመለስ የተካሄደው ጥረት ፍሬ ሳያሳይ ከርሟል። የሃይማኖት አባቶቹ እንደሚገልፁት በፖለቲካ ጣልቃ ገብነት ሳቢያ በተከተለው የቀኖና ጥሰት ቤተ ክርስቲያኒቱ ስትከፋፈል ተከታዮቿንም በየፈርጁ ከፋፍሎ ቆይቷል። ከሁለት ሲኖዶስ ወደ አንድነት መመለሱ እና የተፈጠረው እርቀ ሰላም አንድ ነገር ሆኖ ከሁለት አስርት ዓመታት በላይ የዘለቀው ክፍፍል የፈጠራቸው ክፍተቶች ቀጣይ ተግዳሮት ሊያስከትሉ እንደሚችሉ የሚገምቱ ጥቂት አይደሉም። ዶይቼ ቬለ የቤተ ክርስቲያኒቱ የሃይማኖት አባቶች በጉዳዩ ላይ አወያይቷል። ከድምፅ ዘገባው ያድምጡ፤
ሸዋዬ ለገሠ