1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኢትዮጵያ እና አሜሪካ የጋራ ወታደራዊ ልምምድ ተጀመረ

ሰኞ፣ ሐምሌ 8 2011

የአሜሪካ ጦር ከኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት እና ሌሎች አገሮች ጋር በመሆን ጀስቲፋይድ አኮርድ 2019 የተባለ የ16 ቀናት ወታደራዊ ስልጠና ለመስጠት ያዘጋጀውን መርሃ ግብር ዛሬ በይፋ አስጀምሯል። ስልጠናው በሁርሶ ወታደራዊ ማሰልጠኛ ተቋም ውስጥ የሚሰጥ ነው።

https://p.dw.com/p/3M7SB
Äthiopien Addias Baba | US Militär in Partnerschaft mit Äthiopische Streitkräften und weiteren Organisationen
ምስል DW/S. Mushie

የኢትዮጵያ እና አሜሪካ ወታደራዊ ልምምድ ተጀመረ

የአሜሪካ እና የኢትዮጵያ ጦር በትብብር ያዘጋጁት ወታደራዊ ስልጠና ከ13 ሃገራት የተውጣጡ 1100 የሚሆኑ ሲቪሎች እና ወታደሮች ይሳተፉበታል። ሰልጣኞቹ ይህንን ስልጠና ከወሰዱ በኋላ ወደ የሃገራቸውና ምድብ ስፍራቸው ይመለሳሉ።

ስልጠናው በተለይ የአልሸባብ ስጋት ባጠላበት የምስራቅ አፍሪቃ ቀጣና ያለውን ሰላምና ደህንነት ለማስፈን የሚያስችል ወታደራዊ ክህሎት እና ዝግጁነትን ለማጠናከር ያለመ ነው። አመታዊ እንደሆነ የተነገረለት ይህ ስልጠና ሰላምን በማስፈን ረገድ አለም አቀፍ እና ዘርፈብዙ ልምዶችን ያሻሽላል ተብሏል።

Äthiopien Addias Baba | US Militär in Partnerschaft mit Äthiopische Streitkräften und weiteren Organisationen
ምስል DW/S. Mushie

ወታደራዊ ስልጠናው አስቸጋሪ በሆነ ሁኔታ ውስጥ የሚደረገውን ሽብርን የመዋጋት ተግባር እንደሚያጠናክርም ተገልጿል። ስልጠናው በአፍሪካ ህብረት የሶማሊያ የሰላም ማስከበር ተልእኮን (አሚሶም ) ስራን እንደሚያግዝ ተጠቁሟል።

አሜሪካ ከዚህ በፊት በቁሳቁስ ታደርግ የነበረውን ወታደራዊ ድጋፍ አሁን በእንዲህ ያለ መልኩ ማድረጓ በተለይ ኢትዮጵያ በተባበሩት መንግስታት ስር ለሰላም ማስከበር የምታደርገውን ተሳትፎ ግምት ውስጥ ማስገባቷን አመልካች መሆኑ በመክፈቻው ስነ ስርአት ላይ ተገልጿል።

ሙሉ ዘገባውን ለማድመጥ የድምጽ ማዕቀፉን ይጫኑ። 

ሰለሞን ሙጬ

ተስፋለም ወልደየስ

አዜብ ታደሰ