1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኢንተርኔት አገልግሎት መቆራረጥ መንስኤ

ረቡዕ፣ ሰኔ 26 2011

ኢትዮ ቴሌኮም በሃገሪቱ ተዘግቶ የሰነበተው የ ፊክስድ ብሮድ ባንድ እና የሞባይል ኢንተርኔት የተቋረጠው ሊያስከትል የሚችለውን ጉዳት ግምት ውስጥ በማስገባት ተወስኖ  እንደሆነ  ለዶይቼ ቬለ DW ገለፀተ።  በተገልጋዮች በኩል  ለተፈጠረው  መጉላላት እና  ለደረሰው የኢኮኖሚ  ኪሳራም  ይቅርታ  ጠየቀ።

https://p.dw.com/p/3LX8t
Äthiopien Cherer Aklilu
ምስል Solomon Muchie

ኢትዮ ቴሌኮም ይቅርታ ጠይቋል

 የፊክስድ ብሮድ ናንድ አገልግሎቱ  ከሰኔ 18  ጀምሮ  መለቀቁን  የገለጸው  ኩባንያው  የስልክ  ኢንተርኔት  በአሁኑ  ጊዜ በመላ  ሀገሪቱ  ተለቋል  ብሏል። ዶይቼ ቬለ ባደረገው ማጣራት ግን አሁንም  የስልክ ኢንተርኔት  የማይሠራባቸው የሀገሪቱ  ክፍሎች  መኖራቸውን  ለማወቅ  ተችሏል። ኩባንያው በበኩሉ እንዲህ  ያለው  ችግር  እንዳይደጋገም  ምን ይበጃል  የሚለውን  በመለየት የመፍትሄ  እያፈላለገ መሆኑን ይናገራል። ያነጋገርናቸው ግለሰብ እንዳሉት ከሆነ ግን ችግሩ መነሻው መንግስት ነጻ የሆኑና ሃቀኛ መገናኛ ብዙሃን መፍጠር ባለመቻሉ ሰው ትኩረቱን ማህበራዊ መገናኛዎች ላይ በማድረጉ የመጣ በመሆኑ ሊያስብበት ይገባል ብለዋል። የተጠቃሚዎችን አስተያየት በማካተት ከአዲስ አበባ ሰሎሞን ሙጬ ዝርዝር ዘገባ ልኮልናል።

ሰሎሞን ሙጬ

ሸዋዬ ለገሰ

ኂሩት መለሰ