1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ማሻሻያና የፈጠረዉ መጨናነቅ

ማክሰኞ፣ ሚያዝያ 6 2012

ባንኩ ችግሩ እንዲስተካከል ባለሙያዎቻችን ከፍተኛ ስራ ሰርተዋል ቢልም ደንበኞች ዛሬም ድረስ አገልግሎቱን ለማግኘት ረጃጅም ሰልፍ ይዘው ተስተውለዋል። እንዲህ ያለው አሰራር ለኮሮና ወረርሽኝ ሊያጋልጥ ስለሚችል ባንኩ መላ እንዲፈልግም ደንበኞች ጠይቀዋል።

https://p.dw.com/p/3atVN
Äthiopien Commercial Bank of Ethiopia in Addis Abeba
ምስል DW/E. Bekele

ከሶስት ቀናት መዘጋት በኋላ የተከፈተው ንግድ ባንክ ተጨናንቋል

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የአገልግሎት ማሻሻያ ለማድረግ ባለፈው ሳምንት ከሀሙስ እስከ እሁድ እለት ድረስ መደበኛ የባንክ አገልግሎቱን በማቋረጡ በዚህኛው የሳምንቱ መጀመርያ ቀናት ላይ ከፍተኛ መጨናነቅና ወረፋ አስከትሏል።ባንኩ ችግሩ እንዲስተካከል ባለሙያዎቻችን ከፍተኛ ስራ ሰርተዋል ቢልም ደንበኞች ዛሬም ድረስ አገልግሎቱን ለማግኘት ረጃጅም ሰልፍ ይዘው ተስተውለዋል። እንዲህ ያለው አሰራር ለኮሮና ወረርሽኝ ሊያጋልጥ ስለሚችል ባንኩ መላ እንዲፈልግም ደንበኞች ጠይቀዋል።

ሰለሞን ሙጬ

ታምራት ዲንሳ

ሂሩት መለሰ