የኢትዮጵያ ባሕላዊ ሙዚቃ ከኤሌክትሮኒክስ የሙዚቃ ሥልት ጋር ሲቀየጥ
ሐሙስ፣ ሚያዝያ 17 2011ማስታወቂያ
የኢትዮጵያን ባሕላዊ የሙዚቃ መሣሪያዎችን ከኤሌክትሮኒክስ ሙዚቃ ቅንብር ጋር በማዋሃድ መጫወት ከጀመሩ አራት ዓመታትን አስቆጥረዋል የሙዚቃ ጓድ አባላቱ። የቡድኑ አባላት ኹሉም በወጣትንnm,ት እድሜ ላይ ነው የሚገኙት። አባላቱ፦ ማሲንቆ፣ ዋሽንት፣ ከበሮ ይጫወታሉ፤ በኮምፒውተር ስልት የተቀናበረ የኤሌክትሮኒክስ ሙዚቃን ከባሕላዊ ሙዚቃዎቹ ጋር አዋህደው ይጫወታሉ። የሙዚቃ ቡድኑ ፈረንሳይ ሀገር የሙዚቃ ሥራዎቹን ለማቅረብ ብቅ ባለበት ወቅት የፓሪሱሷ ወኪላችን ሃይማኖት ጥሩነህ አነጋግራቸዋለች።
ሃይማኖት ጥሩነህ
ማንተጋፍቶት ስለሺ
ነጋሽ መሐመድ
ተስፋለም ወልደየስ