1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን ያዘጋጀው ስብሰባ

ረቡዕ፣ ነሐሴ 12 2013

ሰኔ 14 ቀን፣ 2013 ዓ. ም የተከናወነውን አገር አቀፍ ምርጫ የታዘቡ አምስት የሲቪክ ማኅበረሰብ ድርጅቶች በመታዘብ ሂደት የተመለከቷቸው አወንታዊ እና አሉታዊ ክስተቶች ላይ ዛሬ ተወያዩ። የሲቪክ ማኅበራቱ ቀድሞ የነበሩባቸው ተግዳሮቶች አሁን በከፊል የተቀረፉ በመሆናቸው ሰበብ ለማብዛት አይመችም ተብሏል በውይይቱ።

https://p.dw.com/p/3z85T
Äthiopien EHRC  LOGO

«ሰበብ ለማብዛት አይመችም»

ሰኔ 14 ቀን፣ 2013 ዓ. ም የተከናወነውን አገር አቀፍ ምርጫ የታዘቡ አምስት የሲቪክ ማኅበረሰብ ድርጅቶች በመታዘብ ሂደት የተመለከቷቸው አወንታዊ እና አሉታዊ ክስተቶች ላይ ዛሬ ተወያዩ። ሥራቸውን በነፃነት እንዲከውኑ ዕድል መፈጠሩን በአወንታ ያነሱት ሲቪክ ማኅበራቱ በድህረ ምርጫው እና በምርጫው ዕለት የተስተዋሉ ማዋከብ፣ ማንገላታት እና ትንኮሳዎች በቀጣይ በሚደረጉ ምርጫዎች መቀረፍ እንደሚገባቸው ገልፀዋል። የምርጫ ሙሉነት መገለጫዎች ሰብዓዊ መብቶች አለመጣስ እና ሰላማዊነታቸው ብቻ ሳይሆን ፍትሓዊነታቸው የሚለኩባቸው መመዘኛዎች ስላሉ የሲቪክ ማኅበራቱ የተጠቃለለ የምርጫ መታዘብ ሪፖርታቸውን ሲያቀርቡ በዚህ ደረጃ ሊሆን እንደሚገባም በውይይቱ ተጠይቋል። የሲቪክ ማኅበራቱ ቀድሞ የነበሩባቸው ተግዳሮቶች አሁን በከፊል የተቀረፉ በመሆናቸው ሰበብ ለማብዛት አይመችም ተብሏል በውይይቱ። 

ሰለሞን ሙጬ
ማንተጋፍቶት ስለሺ
አዜብ ታደሰ