1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኢትዮጵያ መንግሥት የአውሮጳ ኅብረትን ወቀሰ

ዓርብ፣ የካቲት 5 2013

የኢትዮጵያ መንግሥት በትግራይ ክልል «ሕግ የማስከበር» ያለው ዘመቻን ከጀመረበት ጊዜ አንስቶ የአውሮጳ ሕብረት የሚያሳያቸው አቋሞች ተገቢነት የሌላቸው እና ሚዛናዊነት የጎደላቸው ናቸው ሲል ወቀሰ። እውነታውን ማየት ያልፈለገ፣ አለያም ሆን ብሎ ችላ ያለ ነውም ብሏል።

https://p.dw.com/p/3pHf3
Äthiopien Dina Mufti
ምስል Solomon Muchie/DW

ሕብረቱ የሚያሳያቸውን አቋሞች ተገቢነት የሌላቸው ብሏል

የአውሮጳ ሕብረት ስለ ኢትዮጵያ ትግራይ ክልል ያወጣውን መግለጫ «ቀውስ፣ ረሃብና ችግርን ሆነ ብሎ በረድዔት ስም ለራስ ጥቅም ለማዋል የሚደረግ ነባር ፍላጎት ማሳያ» ብሎታል መንግሥት። ከዚህ በተጨማሪ የመረጃ እጥረት ሕብረቱ ሚዛናዊ ያልሆነ መግለጫ ለማውጣት እንደገፋውም የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ዐስታውቋል። የአውሮጳ ሕብረት ለኢትዮጵያ ለሰብዓዊ ድጋፍ በሚል ይዞት የነበረውን ከፍተኛ መጠን ያለው ገንዘብ ለጊዜው ከመልቀቅ ተቆጥቦ መያዙ ይታወቃል። በሌላ በኩል ኢትዮጵያ በትግራይ ክልል በሚደረገው የሰብዓዊ ድጋፍ ተግባር ላይ ሁሉም  የሕብረቱ ሀገራት ተመሳሳይ አቋም አላቸው ብላ እንደማታምንና ሕብረቱም ስትራቴጂክ አጋሯ መሆኑን አሳውቃለች።

ሰለሞን ሙጬ 

ማንተጋፍቶት ስለሺ

ነጋሽ መሐመድ