1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

መንግሥት ለእርዳታ ድርጅቶች የሰጠው ማስጠንቀቂያ

ዓርብ፣ ሐምሌ 9 2013

መንግሥት ከአንዳንድ እርዳታ ድርጅቶች ጋር አብሮ የመሥራት ሁኔታውን ዳግም እንደሚቃኘው፣ አንዳንዶችንም ከአገር ለማስወጣት የሚያስገድድ ሁኔታ በመፈጠሩ ድርጅቶቹ በእርዳታ እና ሰብዓዊ ተግባራት ላይ ብቻ እንዲንቀሳቀሱ አስጠንቅቋል። ሁለት የዲፕሎማሲ እና የፖለቲካ ሳይንስ አዋቂዎች መንግሥት በተጨባጭ ማስረጃ ተመርኩዞ ውሳኔ ላይ እንዲደርስ ጠይቀዋል።

https://p.dw.com/p/3waHM
Äthiopien | Unruhen | Redwan Hussein, ein Sprecher des Amtes des Premierministers
ምስል Minasse Wondimu Hailu/AA/picture alliance

መንግሥት ለእርዳታ ድርጅቶች የሰጠው ማስጠንቀቂያ

በሰብዓዊ ድጋፍ አቅርቦት ስም ኢትዮጵያ ውስጥ የገቡ ረጂ ድርጅቶች የኢትዮጵያን መንግሥት የማካለብና የማጠልሸት ያለውን ዘመቻ በስፋት መክፈታቸውን መንግሥት ገልጿል።ጉዳዩ በዚህ የሚቀጥል ከሆነ መንግሥት ከአንዳንዶቹ ጋር አብሮ የመሥራት ሁኔታውን ዳግም እንደሚቃኘው፣ አንዳንዶችንም ከአገር ለማስወጣት የሚያስገድድ ሁኔታ በመፈጠሩ ድርጅቶቹ በእርዳታ እና ሰብዓዊ ተግባራት ላይ ብቻ እንዲንቀሳቀሱ አስጠንቅቋል።ዶይቼ ቬለ ያነጋገራቸው ሁለት የዲፕሎማሲ እና የፖለቲካ ሳይንስ አዋቂዎች ኢትዮጵያውያን በአንድነትና በትብብር መቆማቸው የወቅቱ መሰረታዊ ጉዳይ መሆኑን ጠቅሰው መንግሥት አጥፊ ግብረ ሰናይ ድርጅቶችን በተጨባጭ ማስረጃ ተመርኩዞ ውሳኔ ላይ እንዲደርስ ጠይቀዋል።ድርጅቶቹ በጥፋታቸው ቀጥለው መንግሥት ከአገር ካስወጣቸው ግን ኢትዮጵያ ላይ ቀላል የማይባል ዲፕሎማሲያዊ ጫና ይፈጠራል ያሉት ተጠያቂዎቹ ያም ሆኖ ግን ጫናው ከአገር ሉዓላዊነት መከበር ሊበልጥ እንደማይችል ተናግረዋል። ሰሎሞን ሙጬ ከአዲስ አበባ  ዝርዝር ዘገባ አለው 

ሰሎሞን ሙጬ
ኂሩት መለሰ
አዜብ ታደሰ