የኢትዮጵያ ህዝባዊ አብዮታዊ ፓርቲ የወደፊት እቅድ
ሰኞ፣ መስከረም 14 2011ማስታወቂያ
ከአራት አሰርተ ዓመት በላይ በኋላ ወደ ሀገር ቤት የተመለሰው ኢህአፓ በአጭር ጊዜ እቅዱ መሰረት በዓብዮቱ ጊዜ ከኢህአፓ ጋር በተያያዘ ይሰሩ ከነበሩ ህዝባዊ ድርጅቶች ጋር ሲንቀሳቀሱ ጉዳት የደረሰባቸውን አፈላልጎ የችግራቸው ተካፋይ መሆኑን ለመግለጽ እና ለተሰሩ ስህተቶችም ይቅርታ ለመጠየቅ እንደሚፈልግ የከፍተኛው ቡድን መሪ አቶ ማስረሻ ዮሴፍ ለDW ገልጸዋል። በመካከለኛ ጊዜም ፓርቲው ከህብረተሰቡ ጋር በዓላማ እና በፖለቲካ ላይ የተመሰረተ ውይይት እያካሄደ የፖለቲካ ስራውን የመጀመር እቅድ እንዳለውም አቶ ማስረሻ አክለው አስታውቀዋል።
ገበያው ንጉሤ
አርያም ተክሌ
ሸዋዬ ለገሠ