የኢትዮ ቴሌኮም የ3ዓመት ዕቅድ
ዓርብ፣ ነሐሴ 24 2011ማስታወቂያ
የተቋሙም መዳረሻ ያመላክታል የተባለው ይህ ስልት በተያዘው የመንግሥት የበጀት አመት በተቋሙ ላይ የባለቤትነት ለውጥ እንደማያመጣ እና በመንግሥት ይዞታ ሥር እንደሚቆይም ተነግሯል። ይሁንና በሚቀጥሉት አመት የተቋሙ የባለቤትነት ጉዳይ ላይ ሌሎች አካላት እንዲሳተፉበት እንደሚደረግ የድርጅቱ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ወ/ሪት ፍሬህይወት ታምሩ ዛሬ በሰጡት መግለጫ አመልክተዋል።
ኢትዮ ቴሌኮም የዓመቱን የቢዝነስ ዕቅድ ሲያስቀምጥም የደንበኞቹን ቁጥር ከ43.6 ሚሊዮን ወደ 50.4 ፣ የገቡ መጠኑንም በ2011 መጨረሻ አሁን ካለበት 36.3 ቢሊዮን ወደ 45.4 ቢሊዮን ለማሳደግ ማቀዱን አመልክቷል። ተቋሙ እንዳለው የደንበኞች ፍላጎት ከድምፅ አገልግሎት ይልቅ የሞባይል ኢንተርኔት አገልግሎት ላይ እያደገ በመምጣቱ የሚከናወኑ የማሻሻጻ ሥራዎች በዚሁ ላይ የሚያተኩር ይሆናል። የገቢ ምንጬንም አሁን ካሉ በላይ ሌሎች አገልግሎቶችን በማቅረብ ለማሳደግ መወጠኑንም አመልክቷል። ሰሎሞን ሙጬ ከአዲስ አበባ ዝርዝር ዘገባ ልኮልናል።
ሰሎሞን ሙጬ
ሸዋዬ ለገሠ
ተስፋለም ወልደየስ