1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኢሳያስ እና የቢን ዘይድ ዉይይት

ነጋሽ መሐመድ
ማክሰኞ፣ ሰኔ 26 2010

የኤርትራ ማስታወቂያ ሚንስትር አቶ የማነ ገብረ መስቀል በቲዊተር ገፃቸዉ እንደፃፉት ሁለቱ መሪዎች የኤርትራን እና የተባበሩት አረብ ኤምሬቶችን ግንኙነት ለማጠናከር ተስማምተዋል።

https://p.dw.com/p/30laI
Vereinigte Arabische Emirate - Präsident Isaias Afwerki & Kronprinz Sheikh Mohamed Bin Zayed
ምስል Yemane G. Meskel, Minister of Information, Eritrea

የኤርትራዉ ፕሬዝደንት ኢሳያስ አፈወርቂ ከተባበሩት አረብ ኤምሬቶች አልጋወራሽ ከልዑል ሼሕ መሐመድ ቢን ዘይድ ጋር ዛሬ ዱባይ ዉጥት ተገኛኝተዉ ተወያዩ።ፕሬዝደንት ኢሳያስ የተባበሩት አረብ ኤምሬቶችን ለመጎብኘት አቡዳቢ የገቡት ትናንት ነዉ።የኤርትራ ማስታወቂያ ሚንስትር አቶ የማነ ገብረ መስቀል በቲዊተር ገፃቸዉ እንደፃፉት ሁለቱ መሪዎች የኤርትራን እና የተባበሩት አረብ ኤምሬቶችን ግንኙነት ለማጠናከር ተስማምተዋል። ሁለቱ መሪዎች በቅርቡ የተከሰቱ ዓለም አቀፍ እና አካባቢያዊ ፖለቲካዊ ሁኔታዎች በየሐገራቱ ሥለሚኖረዉ ትርጉም አንስተዉ መክረዋል። ኢትዮጵያ እና ኤርትራ የ20 ዓመት ጠባቸዉን ለማብረድ በቅርቡ ተስማምተዋል።የኤርትራ ፕሬዝደንት ኢሳያስ አፈወርቂ እና የኢትዮጵያዉ ጠቅላይ ሚንስትር ዓብይ አሕመድ በቅርቡ ፊትለፊት ተገናኛተዉ ለመወያየት ቀጠሮ አላቸዉ።ለሁለቱ ሐገራት መቀራረብ የሳዑዲ አረቢያ እና የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች መሪዎች አስተዋፅኦ ማድረጋቸዉ በሰፊዉ ይታመናል።

ነጋሽ መሐመድ 

አዜብ ታደሰ