1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

   የኢሰመጉ ሥጋት

ዓርብ፣ ሐምሌ 12 2011

ኢሰመጉ ሰሞኑን ባወጣዉ መግለጫ እንዳለዉ እምና መጋቢት የተጀመረዉ ለዉጥ በአብዛኛዉ ኢትዮጵያዊ  ዘንድ ከፍተኛ ተስፋ ሳያደረ፣ ድጋፍም ያተረፈ ነዉ።ይሁንና መንግስት በቅርቡ የሚወስዳቸዉ እርምጃዎች ጅምሩን ለዉጥ ያደናቅፈዋል የሚል ስጋት አሳድሯል

https://p.dw.com/p/3MKjf
Der Äthiopischer Menschenrechtsrat
ምስል DW/G. Tedla

የኢሰመጉ ሥጋት

የኢትዮጵያ መንግስት «መፈንቅለ መንግሥት» ካለዉ ከሰኔ 15ቱ የባለስልጣናት ግድያ በኋላ ጋዜጠኞችና ተቃዋሚ ፖለቲከኞች መታሰራቸዉ ኢትዮጵያ ዉስጥ ባለፈዉ ዓመት የፈነጠቀዉን የሠላምና የዴሞክራሲ ተስፋ ሊያጨናጉለዉ እንደሚችል የኢትዮጵያ የሰብአዊ መብት ጉባኤ (ኢሰመጉ) አሳሰበ።ኢሰመጉ ሰሞኑን ባወጣዉ መግለጫ እንዳለዉ እምና መጋቢት የተጀመረዉ ለዉጥ በአብዛኛዉ ኢትዮጵያዊ  ዘንድ ከፍተኛ ተስፋ ሳያደረ፣ ድጋፍም ያተረፈ ነዉ።ይሁንና መንግስት በቅርቡ የሚወስዳቸዉ እርምጃዎች ጅምሩን ለዉጥ ያደናቅፈዋል የሚል ስጋት አሳድሯል።

ጌታቸዉ ተድላ ኃይለ ጊዮርጊስ 

ነጋሽ መሐመድ

አዜብ ታደሰ