1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኢሰመጉ ማሳሰቢያ

ሐሙስ፣ ሚያዝያ 14 2013

ኢትዮጵያ ውስጥ እየተፈጸሙ ያሉ የመብት ጥሰቶችን መንግሥት በአስቸኳይ እንዲያቆም የኢትዮጵያ የሰብአዊ መብቶች ጉባኤ (ኢሰመጉ) አሳሰበ። ኢሰመጉ «የሰብአዊ መብቶች ጥሰትን በማስቆም አገርን እንታደግ» በሚል ርእስ ትናንት ባወጣው መግለጫ እና ለዶይቸ ቬለ ዛሬ በሰጠው ተጨማሪ ማብራሪያ የዜጎች ሞት፣ መፈናቀል እና የንብረት መውደም አሳስቦኛል ብሏል። 

https://p.dw.com/p/3sR6u
Logo des Ethiopian Human Rights Council
ምስል Ethiopian Human Rights Council

«የዜጎች ሞት፣ መፈናቀል እና የንብረት መውደም አሳስቦኛል»

ኢትዮጵያ ውስጥ እየተፈጸሙ ያሉ የመብት ጥሰቶችን መንግሥት በአስቸኳይ እንዲያቆም የኢትዮጵያ የሰብአዊ መብቶች ጉባኤ (ኢሰመጉ) አሳሰበ። ኢሰመጉ «የሰብአዊ መብቶች ጥሰትን በማስቆም አገርን እንታደግ» በሚል ርእስ ትናንት ባወጣው መግለጫ እና ለዶይቸ ቬለ ዛሬ በሰጠው ተጨማሪ ማብራሪያ የዜጎች ሞት፣ መፈናቀል እና የንብረት መውደም አሳስቦኛል ብሏል። 

በተመሳሳይ የኢትዮጵያ የሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ)ትናንት ባወጣው መግለጫ፦ በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ከማሺ ዞን የሚገኘውና ከሃያ አምስት ሺህ በላይ ነዋሪዎች የሚገኙበት የሴዳል ወረዳ ሙሉ በሙሉ ሊባል በሚችል ደረጃ ከሚያዝያ 11 ቀን፣ 2013 ዓም ጀምሮ በታጣቂዎች ቁጥጥር ስር መዋሉን የደረሱት መረጃዎች እንደሚያመላክቱ ገልጧል። ታጣቂዎች በወረዳው ግድያዎች ፈጽመው ቤቶች፣ ንብረቶች እና የተለያዩ ተቋማታን ማቃጠላቸውን ዶይቸ ቬለ ትናንት መዘገቡ ይታወሳል።  

ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር  
ማንተጋፍቶት ስለሺ
እሸቴ በቀለ