የኢሕአዴግ ጉባኤ
ረቡዕ፣ መስከረም 23 2011ማስታወቂያ
የኢትዮጵያ ገዢ ፓርቲ፣ የኢትዮጵያ ሕዝብ አብታዊ ግንባር (ኢሕአዴግ) 11ኛ ጉባኤ ዛሬ ሐዋሳ ዉስጥ ተጀምሯል። የዘንድሮዉ ጉባኤ 27 ዓመት በዘለቀዉ የኢሕአዴግ አገዛዝ፣ ግንባሩ ለየት ያለ ያመራር እና የፖለቲካ ለዉጥ ባደረገበት እና ኢትዮጵያ በተለያዩ አካባቢዎች በሚደረጉ የጎሳ ግጭቶች በሺ የሚቆጠሩ ዜጎችዋ በሚገደሉ እና በሚፈናቀሉበት ወቅት የተደረገ ነዉ። አዲሱ የግንባሩ ሊቀመንበር እና የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ አሕመድ ለጉባኤተኞች እንደገሩትም ግጭት ጥፋቱ ሁሉንም ኢትዮጵያዊ የሚጎዳ ነዉ። በተለይ ከደቡብ፤ ከኦሮሞ እና ከአማራ ፓርቲዎች አዳዲስ ፖለቲከኞች የተቀየጡበት ጉባኤ እስከፊታችን አርብ በዝግ ይመክራል።
ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር
ነጋሽ መሐመድ
አዜብ ታደሰ