1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የአፍሪካ ዉስጥ ግጭቶች በመያዶች ላይ ያሳደረዉ ተጽኖ

ቅዳሜ፣ ነሐሴ 22 2013

ካሜሩን እና ኢትዮጵያ ባለፉት ወራት በየሃገራቸዉ የዓለም አቀፍ የእርዳታ ድርጅቶችን እንቅስቃሴን ገድበዋል። ግደባዉ ለሲቪሉ ነዋሪ አሉታዊ ውጤትን ሊያስከትል ይችላል።  መንግሥታዊ ያልሆኑ የርዳታ ድርጅቶችን ከማገዱ ዉሳኔ ጀርባ ያለ ነገር ይኖር ይሆን?

https://p.dw.com/p/3zZpG
Ärzte ohne Grenzen | Krise in Zentralmali
ምስል Mohamed Dayfour/MSF

የተመድ የኢትዮጵያ መንግሥት መያዶችን እንዲያግዝ ጥሪ አቅርቦአል

ካሜሩን እና ኢትዮጵያ ባለፉት ወራት በየሃገራቸዉ የዓለም አቀፍ የእርዳታ ድርጅቶችን እንቅስቃሴን ገድበዋል። ግደባዉ ለሲቪሉ ነዋሪ አሉታዊ ውጤትን ሊያስከትል ይችላል።  መንግሥታዊ ያልሆኑ የርዳታ ድርጅቶችን ከማገዱ ዉሳኔ ጀርባ ያለ ነገር ይኖር ይሆን? የዶቼ ቬለዋ ማርቲና ሺኮቭስኪ፤ በኢትዮጵያ እና በካሜሩን መንግሥታዊ ያልሆኑ ርዳታ ድርጅቶች የሚደርስባቸዉ ጫና ስትል ተከታዩን ዘገባ ሰሞኑን ለአንባብያን አቅርባለች።

የእርዳታ ድርጅቶች በአፍሪቃ ሃገራት ዉጥረት በሚታይባቸዉ ቀጠናዎች ውስጥ ከፍተኛ ጫና እየደረሰባቸው ነው። ስትል ትጀምራለች የዶቼ ቬለዋ ማርቲና ሺኮቭስኪ።  ለምሳሌ በማዕከላዊ አፍሪቃ በምትገኘዉ በካሜሩን ውስጥ በያዝነዉ ነሐሴ ወር ዉስጥ ድንበር የለሹ የሃኪሞች ቡድን በምህፃሩ  (MSF) የተባለዉ መንግሥታዊ ያልሆነ የርዳታ ድርጅት ይሰራበት ከነበረዉ ከሰሜን-ምዕራብ ካሚሩን ተነስቶአል አልያም እንዳይሰራ ታግዶአል።

Kamerun Mitglieder der Gendarmerie
ምስል Marco Longari/AFP/Getty Images

ታዛቢዎች እንደሚሉት የካሜሩን መንግሥት  (MSF) የተባለዉን መንግሥታዊ ያልሆነ የርዳታ ቡድን ከስራ ካገደ በኋላ በሃገሪቱ ዉስጥ የሚታየዉ አስከፊ የሰብአዊ ጉዳይ ፤ ይበልጥ እንዳይባባስ ያሰጋል። ለበርካታ ዓመታት በሰሜን ምዕራብ ካሜሩን በመንግስት ወታደሮች እና በክልሉ ነፃነትን እናመጣለን በሚሉ ተገንጣዮች መካከል ደም አፋሳሽ ግጭት ሲካሄድ ቆይቷል።

ብዙ ሆስፒታሎች ወድመዋል

በዚሁ በሰሜን ምዕራብ ካሜሩን በሚካሄደዉ ግጭት እና ጦርነት ሆስፒታሎች በቃጠሎ ወድመዋል፤ በህክምና ጣብያዎች የሚሰሩ የጤና ባለሞያዎች ግጭቱን ሸሽተዉ ከአካባቢዉን ጥለዉ ለቀዋል። በአሁኑ ወቅት በካሜሩን የገጠር አካባቢዎች የሚንቀሳቀሱ ጥቂት የመንግሥት ጤና ጣቢያዎች እና የኃይማኖት ተቋማት ሆስፒታሎች ማለት የሚስዮን ሆስፒታሎች ብቻ ናቸው ሲል የዶቼ ቬለ  (DW) የካሜሩን  ዘጋቢ ዣን ማሪ ሶንግ ይናገራል።

ሰሜን-ምዕራብ ካሚሩን በነበረዉ የእርስ በርስ ግጭት ምክንያት ጉዳት የደረሰባቸዉ ሆስፒታል ዉስጥ ርዳታን ቢያገኙም ብዙ ሰዎች ግን ለሆስፒታሉ ሂሳቡ ማወራረድ  አልቻሉም። የበካሜሩን ሰሜን ምዕራብ ላይ የምትገኘዉ የባሜንዳ ከተማ ሆስፒታል ኃላፊ ዴኒስ ንሳሜ ለድንበር የለሹ የሃኪሞች ቡድን  እንደገለፁት “የድንበር የለሹ የዶክተሮች ቡድን ከአካባቢዉ ላይ መውጣት በሆስፒታላችን ላይ ሸክሙን በእጥፍ እንዲጨምር አድርጎአል ሲሉ የዶቼ ቬለ ተናግረዋል።

„ከጎርጎረሳዊዉ 2018 ጀምሮ ለሆስፒታሉ አገልግሎት ያልተከፈለ  72 ሚሊዮን ፍራንክ አለ። በሆስፒታሉ የታከሙት በድንገተኛ አደጋዎች የቀዶ ሕክምና  ያገኙ ፣  በጠመንጃ ጥይት እና በመንገድ ትራፊክ አደጋዎች ህክምና የተደረገላቸዉ ናቸዉ። ነገር ግን ሂሳቡን አልከፈሉም"

በሰሜን-ምዕራብ ካሚሩን ባሜንዳ ከተማ ከሚኖሩ እንደ ጆሴፍ ንፎር ላሉ ሰዎች ፣ የ(MSF)ማለትም እንደ ድንበር የለሽ የሃኪሞች ቡድን ከአካባቢዉ ላይ መውጣት ትልቅ ችግር ብሎም ውድቀት ነው። አቶ ጆሴፍ ንፎርን ይረዳ የነበረዉ ልጃቸዉ በአንድ ወታደር ተሽከርካሪ ተገጭቶ ተገድሎባቸዋል። ጆሴፍ በሆስፒታል ለህክምና ብዙ ገንዘብን አጥፍተዋል። አሁን ግን የሚረዳቸዉ ልጅም ስለሌላቸዉ በድንበር የለሹ የሐኪሞች ድርጅት ተስፋ አድርገዉ ነበር።

«በሆስፒታል ብዙ ህክምናን አድርጌያለሁ ። ገንዘቤንም የጨረስኩት ብዙ ምርመራና ህክምናን በማድረጌ ነዉ። ምንም የቀረኝ ነገር የለም።  የተዋወክዋቸዉ የህክምና ዶክተሮችም  የምኖርባትን ባሜንዳ ከተማን ጥለዉ ወጥተዋል። በእዉነቱን ያለኝን ገንዘብ ሁሉ አሟጥጬ ጨርሻለሁ፤ ለሆስፒታል የምከፍለዉ ምንም ፍራንክ የለኝም»

አምቡላንስ ከአሁን በኋላ አይመጣም

ነፍሰ ጡርዋ ካሜሩናዊ ማርሴሊን ቲሲሚ እስከባለፈዉ ታህሳስ ወር ድረስ በድንበር የለሽ ዶክተሮች ቡድን ርዳታን አግኝተዋል፤ የድርጅቱ ተጠቃሚም ነበሩ። ልጃቸዉን ለመገላገል ምጣቸዉ ሲመጣ ግን እቤታቸዉ አልጋ ላይ ነበሩ ። ወደ አካባቢዉ ሆስፒታልም እንዳይሄዱ የአካባቢያቸዉ የፀጥታ ሁኔታ አስተማማኝ አልነበረም።

 “ምሽት ላይ ምጤ መጣ። ወደ ሆስፒታል እንድሄድ ሁሉ ሰዉ ሁሉን አማራጭ ሞከረ። ነገር ግን አካባቢዉ ላይ ከፍተና የፀጥታ ስጋት ስለነበር ሆስፒታል መሄድ አልቻልኩም። ከዝያም ብዙዎቹ ጎረቤቶቼ ወደ ድንበር የለሹ የሃኪሞች ድርጅት እንድደዉል እና እንድጠራቸዉ ሃሳብ አቀረቡልኝ። ከዝያም እንደተባለዉ ወደ (MSF) ደወልኩ።  በአጭር ጊዜ ውስጥ መጥተዉ ወደ ቅድስት ማርያም ሆስፒታል ወሰዱኝ ፣ ብዙ  እንክብካቤ አደረጉልኝ ። ልጄንም በሰላም ለመገላገል በቃሁ»

Symbolbild | Unfall in Kamerun | Knapp 40 Tote
ምስል Joel Kouam/AP Photo/picture alliance

ከታህሳስ 2020 ጀምሮ (MSF)ማለትም ድንበር የለሹ የሐኪሞች ድርጅት በመንግስት ትእዛዝ መሰረት በሰሜን-ምዕራብ ካሚሩን  ከሚያደርገው የርዳታ እንቅስቃሴ ሁሉ ታግዶአል። ለእገዳዉ የተሰጠዉ ምክንያት ደግሞ ከሃገሪቱ የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ጋር የሚያደርገዉን የትብብር ማዕቀፍ በቅድሚያ ማብራራት ያስፈልገዋል የሚል እንደሆነ  (MSF)ለዶቼ-ቬለ በፁሁፍ አሳዉቆአል።  ይሁንና ድርጅቱ በጽሑፉ አያይዞ እንደጠቀሰዉ፤ ይፋዊ ባልሆነ በመንገድ በካሜሩን መንግሥት የተጠረጠርንበት ጉዳይ ሌላ ነዉ ብሎአል። ይኸዉም   “እኛ የተጠረጠርነዉ ይላል፤ ድንበር የለሹ የሐኪሞች ድርጅት። እኛ የተጠረጠርነዉ « በሃገሪቱ በሰሜን ምዕራብ ክፍል ላይ ከሚገኙ የታጠቁ ቡድኖች ጋር በጣም ቅርበት እንደምንሰራ እና እንደዉም እኛ ለነሱ እያሴርን እንደሆነ ነዉ በመታመኑነዉ» ሲል ድርጅቱ አያይዞ ለዶቼ ቬለ በፅሑፉ አሳዉቋል። ይሁንና ድንበር የለሹ ሃኪሞች ድርጅት በካሜሩን መንግሥት የደረሰበትን ውንጀላ ለማስተባበል በግልፅ ስራዉን ለማሳየት እና ለማስረዳት ቢሞክርም ተቀባይነትን አላገኘም ወይም አልተሳካለትም። 

በተመሳሳይ በቡሩንዲ በጎርጎረሳዉያኑ 2019 “ሃንድካፕ ኢንተርናሽናል” በምህጻሩ (HI) የተሰኘዉ የእርዳታ ድርጅት ከመንግስት በተሰጠው መመሪያ፤ ከ 26 ዓመታት በኋላ ሥራውን አቁሞአል። የቡሩንዲ መንግሥት በሃገሪቱ የሚገኙ ሁሉም የውጭ እርዳታ ድርጅቶች 60 በመቶ የአካባቢውን ሠራተኞች  ከሁቱ ብሔረሰብ ፣ 40 በመቶውን ደግሞ ከቱሲዎች እንዲቀጥሩ ጠይቆ ወይም መመርያ አዉጥቶ ነበር። ይሁንና (HI) ማለትም “ሃንድካፕ ኢንተርናሽናል” የተባለዉን ጨምሮ ሁሉም የዉጭ ርዳታ ድርጅቶች ቦታዉን ለቀዉ ወጥተዋል።  

የተሳሳተ መረጃ እየተሰራጨ ነዉ?

ወደ ሌላ መንግሥታዊ ያልሆኑ የርዳታ ድርጅቶች ጉዳይ ስናልፍ ደግሞ ትላለች ፀሃፊዋ ማርቲና ሺኮቭስኪ፤ በኢትዮጵያ ያለዉ ሁኔታ ነዉ። የኢትዮጵያ መንግሥት በሐምሌ ወር የኖርዌይ ስደተኞች ካውንስል በምህፃሩ(NRC) የሆነዉን መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች በሙሉ፣ የሆላንድን ድንበር የለሹን የሃኪሞች ድርጅት በምህጻሩ (MSF)እና አል ማክቶሜ ፋውንዴሽን የተባሉ የርዳታ ድርጅቶችን ለሦስት ወራት ያህል ሥራቸውን አቋርጠዋል። የርዳታ ድርጅቶቹ ስራቸዉንን እንዳይሰሩ የተወነጀሉበት ምክንያት  ያለ ሥራ ፈቃድ የውጭ ሠራተኞችን ቀጥረው በማኅበራዊ ሚዲያ ላይ የሐሰት መረጃን አሰራጭተዋል በሚል ነዉ። በማኅበራዊ መገኛኛ ዘዴዎች መንግሥንም ሆነ የህወሓት ቡድንን በመንቀፍም ሆነ በመደገፍ የሚሰራጨዉ የተለያየ ፕሮፖጋንዳ በትግራይ ጦርነት ከተቀሰቀሰ ወዲህ እያየለ መጥቶአል። የዶቼ ቬሌ አምደና እና የፖለቲካ ጉዳዮች ተንታኝ አቶ በፈቃዱ ኃይሉ እንደሚሉት፤ የኢትዮጵያ መንግሥት በፕሮፖጋንዳ ጦርነቱ እየተበለጥኩ ነዉ የሚል  የሚል ሥጋት አለበት የሚል ጥርጣሬ እንዳላቸዉ ይናገራሉ።

Tigray Konflikt | Äthiopien Eritrea Flüchtlinge
ምስል Ben Curtis/AP Photo/picture alliance

«የኢትዮጵያ መንግሥት የፕሮፖጋንዳ ጦርነቱን እየተበለጥኩ ነዉ የሚል ስጋት አለበት ምክንያቱም ጦርነቱ በሪት ላይ ቢሆንም ፤ በትርክ ግን የመበላለጥ ነገር አለ። የዓለም አቀፍ ድጋፍ ወይም ተቃሞ በትርክሩን ተከትሎ ነዉ ማለት ነዉ። እና የኢትዮጵያ መንግሥት፤  ህወሃት በትርክት በልጦኛል ብሎ ያምናል ብዬ አምናለሁ ። ስለዚህ ደግሞ የዓለም አአፉ የሲቪል ድርጅቶች አለበት ብሎ ያምናል ምክንያቱም ፤ እነሱ የሚያወጥዋቸዉ  መግለጫዎች እና ማሳሰብያዎች የህወሓትን አጀንዳ እያራመዱ ይመስለዋል። በጣም ድንጉጥ የሆነ ምላሽ እየሰጠ ያለዉ ለዚህ ነዉ።»   

መንግሥታዊ ያልሆኑ የርዳታ ድርጅቶች መባረር በሃገሪቱ ምናልባትም የተፈናቃዮችን ቁጥር ሊጨምር ይችላል፤ የሚል አስተያየትም በዘገባዉ ተካቶአል።   

እንደ ተባበሩት መንግሥታት መግለጫ ከሆነ በትግራይ ከአምስት ሚሊዮን በላይ የሆነዉ ነዋሪ ራሱን መመገብ በማይችልበት ደረጃ ላይ ይገኛል።  በዚህም ምክንያት የመንግሥታቱ ድርጅት ሐምሌ ወር ላይ ከመንግሥት ተጨማሪ ርዳታ እንዲሰጥ  መጠየቁን የተመድ ቃል አቀባይ ተናግረዉ ነበር።    

«ለኢትዮጵያ መንግስት የምናቀርበዉ ተጨባጭ የሆነ አንድ ጥያቄ አለን። ይኸዉም መንግስት ለሰብአዊ ርዳታ አቅራቢዎች ተጨማሪ የግንኙነት መሳሪያዎችን ይዘው እንዲመጡ እና መንግስታዊ ላልሆኑ ሠራተኞች የረጅም ጊዜ የመኖርያ ፈቃድ ማለትም «ቪዛ» እንዲፈቅድ ነዉ። ይህ አሳሳቢ እና ወሳኝ ወሳኝ ጉዳይ ነው። ችግሮችን ለመቅረፍ እና ስራችን ለማከናወን እነዚህ ነገሮች ያስፈልጉናል።»

ማርቲና ሺኮቭስኪ / አዜብ ታደሰ