የአፍሪቃውያን ስደተኞች ሰቆቃ በሊቢያ
ማክሰኞ፣ ታኅሣሥ 3 2010ማስታወቂያ
ይኸው በሊቢያ የሚካሄደው የባርያ ንግድ በተለይ ካለፉት ጥቂት ጊዚያት ወዲህ የመገናኛ ብዙኃንን ትኩረት አግኝቷል። ባለፈው ሳምንት በኮት ዲቯር የአቢዦ ከተማ የተሰበሰቡት የአፍሪቃ እና የአውሮጳ መሪዎችም ይህንኑ በስደተኞች ላይ እየደረሰ ያለውን ኢሰብዓዊ ድርጊት እና የመብት ጥሰት ለማብቃት ስምምነት መድረሳቸው ይታወሳል። በተለያዩ አስገዳጅ ሁኔታዎች ከሀገር ቀያቸው የተሰደዱ አፍሪቃውያን ከአስቸጋሪው የሰሀራ በረኃ ጉዞ በኋላ ፣ በሊቢያ የሕገ ወጥ ሰው አሸጋጋሪዎች የባርነት ቀንበር ውስጥ ወድቀዋል፣ አሁን በፈረንሳይ ተገን የጠየቀ አንድ ኢትዮጵያዊ ስደተኛም ራሱ የሕገ ወጥ ሰዎች አሸጋጋሪዎች የባርነት ቀንበር ሰለባ እንደነበር ለዶይቸ ቬለ ገልጿል።
ሀይማኖት ጥሩነህ
አርያም ተክሌ