1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የአፍሪቃ ቀንድ ጸጥታና የፖለቲካ ውጥረት

እሑድ፣ ታኅሣሥ 25 2013

የአፍሪቃው ቀንድ የጸጥታ ኹናቴ እና የፖለቲካ ውጥረት ከቅርብ ጊዜያት አንስቶ የተካረረ ይመስላል። የኢትዮጵያ እና የሱዳን የድንበር ግዛት ይገባኛል ውዝግብ ብዙ ዓመታት ቢያስቆጥርም የሰሞኑን ያህል ተባብሶ ዐያውቅም። እንያውም የሱዳን ታጣቂዎች በድንበር ይገባኛል ጥያቄ ወደ ኢትዮጵያ ግዛት ዘልቀው መግባታቸው ተዘግቧል።

https://p.dw.com/p/3nQqG
Infografik Karte Grand Ethiopian Renaissance Dam ENG

የአፍሪቃው ቀንድ ውጥረት

የአፍሪቃው ቀንድ የጸጥታ ኹናቴ እና የፖለቲካ ውጥረት ከቅርብ ጊዜያት አንስቶ የተካረረ ይመስላል። የኢትዮጵያ እና የሱዳን የድንበር ግዛት ይገባኛል ውዝግብ ብዙ ዓመታት ቢያስቆጥርም የሰሞኑን ያህል ተባብሶ ዐያውቅም። እንያውም የሱዳን ታጣቂዎች በድንበር ይገባኛል ጥያቄ ወደ ኢትዮጵያ ግዛት ዘልቀው መግባታቸው ተዘግቧል። ኢትዮጵያ ጉዳዩን በዲፕሎማሲ ለመፍታት ጥረት እንደምታደርግ ኾኖም የሱዳን ባለሥልጣናት ጭምር በጥቃቱ እጃቸው እንዳለበት ገልጣለች። ከድንበሩ ውዝግብ ባሻገር የሕዳሴ ግድብ ላይ ፍላጎት ያላቸው ሃገራት ከጀርባ ግፊት እያደረጉ እንደኾነም ይጠቀሳል።

ሱዳን እና ደቡብ ሱዳንም ዘላቂ የሚባል ሰላም በመካከላቸው የለም። በሌላ አቅጣጫ፤ ግን ደግሞ በተቀራራቢ ጊዜያት ጎረቤት ኬንያ እና ሶማሊያ በድንበር ይገባኛል ፍጥጫ ተወዛግበው ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነታቸውን እስከማቋረጥም መድረሳቸው ተሰምቷል። የምሥራቅ አፍሪቃ የልማት በይነ-መንግሥታት (ኢጋድ) አባል ሃገራት መሪዎች 38ኛ ልዩ ጉባኤ ከዐሥራ አምስት ቀናት በፊት ጅቡቲ ውስጥ ሲደረግ ይኸው ውጥረት ተስተውሏል። ከስብሰባው ተሳታፊዎች መካከል የአፍሪቃ ኅብረት ኮሚሽን ሊቀ-መንበር ሙሳ ፋኪ ማሕማት፦ ቀጣናው «ራሱን በፈታኝ ሁኔታ ውስጥ አግኝቶታል። ኢጋድም በርካታ ፈተናዎች ገጥመውታል» ሲሉ አካባቢው ላይ ስለተጋረጠው ፈታኝ ኹኔታ አሳስበዋል።

በአፍሪቃው ቀንድ በየሀገራቱ ውስጥ ከሚታዩ የፖለቲካ ውጥረቶች ባሻገር በአካባቢው ላይ የተለያዩ የውጭ ኃይላት ልዩ ፍላጎት እንዳላቸውም ይስተዋላል። ዶቼ ቬለ (DW) በአፍሪቃው ቀንድ የታየው ውጥረት ላይ ዳሰሳ በማድረግ የውጥረቱ ማርገቢያ መፍትኄ ላይ ያተኮረ ውይይት አካሂዷል።

ሙሉውን ውይይት የድምጽ ማዳመጫውን በመጠቀም ማድመጥ ይቻላል። 

ማንተጋፍቶት ስለሺ

ነጋሽ መሐመድ