የአፍሪማ የሙዚቃ አሸናፊ ቤቲ ጂ
እሑድ፣ ኅዳር 23 2011ማስታወቂያ
ከሁለት ዓመት በፊት ለአድማጮች ያቀረበችው የመጀመሪያ አልበሟ ማነው ፍፁም የሙዚቃውን ገበያ የተቀላቀለችው የዛሬዋ የመዝናኛ እንግዳችን ብሩክታዊት ጌታሁን (ቤቲ ጂ) በአምስተኛው የመላው አፍሪማ የሙዚቃ ሽልማት ላይ ተሳትፋ በስድስት ዘርፍ ታጭታ በሶስት አሸንፋ ወደ ሀገሯ ተመልሳለች። ከዚህ በፊት በዚህ አህጉራዊ ውድድር ላይ ሀመልማል አባተ፣ ሔኖክና መሃሪ ወንድማማቾችና፣ ፀደኒያ ገብረ ማርቆስ ተሳትፈው፤ ሀመልማል አባተ በባህል ዘርፍ እና ፀደኒያ ገብረ ማርቆስ ደግሞ በዘመናዊ ሁለቱም የምስራቅ አፍሪካ ምርጥ ሴት ድምፃውያን ተብለው ተሸልመው ተመልሰዋል። በዘንድሮው የአፍሪማ ሽልማት ላይ ሌላዋ ሴት ኢትዮጵያን ወክላ ቀርባ የነበረው ዲጄ ሊ እቴጌ በተሰኘው ሙዚቃዋ በምርጥ ሴት አፍሪካዊ አነቃቂ አርቲስት ዘርፍ ተወዳድራ የነበረ ሲሆን ውጤት ሳይቀናት ግን ቀርቷል። በዛሬው የመዝናኛ ዝግጅታችን የብራስልሱ ዘጋቢያችን ዳግማዊ ሲሳይ ተድላ ከአመቱ የአፍሪቃ ምርጥ አልበም ባለድል ቤቲ ጂ እና ከስራ አስኪያጇ እዮብ አለማየሁ ጋር ያደረገውን ዝግጅት ይዞልን ቀርቧል።
ዳግማዊ ሲሳይ ተድላ
ልደት አበበ