የአፋር ክልል ስሞታ
ማክሰኞ፣ ሐምሌ 20 2013ማስታወቂያ
ሕዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ (ሕወሓት) በሚቆጣጠራቸዉ የአፋር ክልል ወረዳዎች የሚኖረዉን አርብቶ ደር ሕዝብ እየበደለ፣ ሐብትና ንብረትም እየዘረፈ ነዉ በማለት የአፋር ክልል መስተዳድር ወቀሰ። የክልሉ የኮሙኒኬሽን ፅሕፈት ቤት ኃላፊ አሕመድ ከሎይታ እንደሚሉት የሕወሓት ታጣቂዎች በተቆጣጠሯቸዉ አካባቢዎች ይኖር የነበረ 75ሺሕ ሕዝብ ከቤት ንብረቱ ተፈናቅሏል። ሕወሓት እስካለፈዉ ሳምንት ድረስ ከአፋር ክልል 4 ወረዳዎችን መቆጣጠሩን አቶ አሕመድ አረጋግጠዋል። በተያያዘ ዜና ሰሞኑን በአፋርና በሶማሌ ክልል አዋሳኝ ድንበር አካባቢ ተቀስቅሶ የነበረዉ ግጭት መቆሙን የአፋር ባለስልጣናት አስታዉቀዋል።
ሰለሞን ሙጬ
ነጋሽ መሐመድ
ሸዋዬ ለገሠ