1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የአፋር ህዝብ መሪ የሆኑት ሱልጣን ሀንፍሬ አሊሚራህ አረፉ

እሑድ፣ መስከረም 10 2013

የአፋር ህዝብ መሪ  ሱልጣን ሀንፍሬ አሊሚራህ አረፉ፡፡ የአፋር ሱልጣን ሀንፍሬ አሊሚራህ ባደረባቸው የሳንባ ምች ህመም በአዲስ አበባ ሲልክ ሮድ እና ሃሌሉያ ሆስፒታሎች ለ17 ቀናት ያህል የህክምና ክትትል ሲያደርጉ ከቆዩ በኋላ ነው ትናንት ሌሊቱን 9፡30 ገደማ በ71 ዓመታቸው ከዚህ ዓለም በሞት መለየታቸው የተሰማው።

https://p.dw.com/p/3ikuw
Äthiopien Sultan Hanfare Ali Mirah
ምስል Privat

የአፋር ህዝብ መሪ  ሱልጣን ሀንፍሬ አሊሚራህ አረፉ፡፡ የአፋር ሱልጣን ሀንፍሬ አሊሚራህ ባደረባቸው የሳንባ ምች ህመም በአዲስ አበባ ሲልክ ሮድ እና ሃሌሉያ ሆስፒታሎች ለ17 ቀናት ያህል የህክምና ክትትል ሲያደርጉ ከቆዩ በኋላ ነው ትናንት ሌሊቱን 9፡30 ገደማ በ71 ዓመታቸው ከዚህ ዓለም በሞት መለየታቸው የተሰማው። ከ2004 ዓ.ም. ጀምሮ ሕይወታቸው እስካለፈበት ዕለት ድረስ የአፋር ህዝብ ሱልጣን በመሆን ያገለገሉት ሱልጠን ሀንፍሬ አሊሚራህ ቀደም ሲል የአፋር ክልል ፕሬዝዳንት እንዲሁም በኩዌት የኢትዮጵያ አምባሳደር ሆነው አገራቸውን አገልግለዋል፡፡ የሱልጣን ሀንፍሬ ስርዓተ ቀብር በነገው ዕለት መስከረም 11 ቀን 2013 ዓ.ም በቀድሞ የክልሉ ዋና ከተማ አሳይታ በሀደሌ ጌራ እንደሚፈጸም ወንድማቸው ኦማር አሊሚራህ ለዶይቼ ቬለ ተናግረዋል፡፡በኢትዮጵያ መጣ ከተባለው ለውጥ አስቀድሞ በሃገሪቱ የፖለቲካ ጉዞ ደስተኛ እንዳልነበሩ የሚነገረው ሱልጣን አንፍሬ አሊሚራህ ከዶ/ር ዐቢይ አህመድ የለውጥ አመራር በኋላ ወደ ሀገር ቤት ተመልሰዋል፡፡ ሱልጣን አንፈሬ አሊሚራህ የሁለት ወንዶችና አምስት ሴት ልጆች አባት ነበሩ፡፡

ስዩም ጌቱ

ታምራት ዲንሳ