1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የአጣዬ ግጭት ያስከተለው ጉዳት

ሐሙስ፣ መጋቢት 16 2013

በአማራ ክልል የኦሮሞ ብሔረሰብ ልዩ ዞን እና በክልሉ የሰሜን ሸዋ ዞን አስተዳደሮች አዋሳኝ አካባቢ ባለፈው ሳምንት ማገባደጃ የተቀሰቀሰው ግጭት አሁን ላይ ወደ አንጻራዊ ሰላም መመለሱን የሁለቱ ዞን አስተዳደሮች ገለፁ፡፡

https://p.dw.com/p/3r8jM
12.06.2013 DW Online Karten Basis Äthiopien Englisch

የአጣዬ ግጭት ያስከተለው ጉዳት

በአማራ ክልል የኦሮሞ ብሔረሰብ ልዩ ዞን እና በክልሉ የሰሜን ሸዋ ዞን አስተዳደሮች አዋሳኝ አካባቢ ባለፈው ሳምንት ማገባደጃ የተቀሰቀሰው ግጭት አሁን ላይ ወደ አንጻራዊ ሰላም መመለሱን የሁለቱ ዞን አስተዳደሮች ገለፁ፡፡
አስተዳዳሪዎቹ ለዶይቼ ቬለ እንዳረጋገጡትም ከትናንት ጀምሮ የኩስ ድምጾች በእጅጉ ቀንሰው ተስተውሏል፤ አንጻራዊ ሰላም በመስፈኑም ህብረተሰቡ ወደ ኑሮ እንቅስቃሴው በከፊል ተመልሷል፡፡
ይሁንና በግጭቱ የደረሰው ጉዳት ከፍተኛ በመሆኑ በሁለት ወረዳዎች አስር ገደማ ቀበሌያት የተፈናቀሉ ዜጎች አስከፊ በተባለ ሁኔታ ላይ ናቸው ተብሏል፡፡
አካባቢውን በማረጋጋት የግጭቱ መነሻ እና በሰው ህይወትና ንብረት ላይ የደረሰውን ውድመት የሚያጣራ የፌዴራሉ መንግስት የፀጥታ እና መርማሪ ቡድን ስራውን መጀመሩም በአስተዳዳሪዎቹ ተነግሯል፡፡
አስተያየታቸውን ለዶይቼ ቬለ ያጋሩት የወሎ ኦሮሞ አባገዳ አህመድ መሃመድ ዑመር የተጣራ ባሉት መረጃቸው በግጭቱ የ60 ሰዎች ህይወት ሲቀጠፍ ከ100 በላይ ቆስለዋል፤ ከ200 ቤቶች የሚልቀው ደግሞ በእሳት ጋይተዋል፡፡

ስዩም ጌቱ 
ነጋሽ መሐመድ