«አዴፓና ሕወሐት መነጋገር አለባቸዉ» ሙሁራን
ረቡዕ፣ ሰኔ 5 2011ማስታወቂያ
የአማራ መስተዳድር እና የትግራይ መስተዳድር ገዢ ፓርቲዎች የገጠሙትን ዉዝግብ ፊት ለፊት ተነጋግረዉ እንዲያስወግዱ ሁለት ምሑራን መከሩ። የባሕር ዳር እና የመቀሌ ዩኒቨርሲቲ ምሑራን እንደሚሉት የአማራ ገዢ ፓርቲ (አዴፓ) እና የትግራይ አቻዉ (ሕወሐት) የገጠሙት ጠብ የሁለቱን ተጎራባች አካባቢዎች ሕዝብ እያጋጨ ነዉ። ምሑራኑ ለዶይቼ ቬለ (DW) እንደነገሩት የፓርቲዎቹ መሪዎች በሽማግሌ፣ በሃይማኖት መሪ እና በስማ በለዉ አማካይነት ከመነጋገር ይልቅ ራሳቸዉ ፊት ለፊት መነጋገር ይገባቸዋል።
ዓለምነዉ መኮንን
ነጋሽ መሐመድ
አዜብ ታደሰ