የአዴፓ እና አዴኃን ውሕደት
ማክሰኞ፣ ኅዳር 4 2011ማስታወቂያ
አዴፓ እና አዴኃን ወደአንድነት መምጣት መቻላቸው ጠንካራ አንድነት ለመፍጠር ጉልህ ድርሻ ይኖረዋል ያሉት አቶ ምግባሩ ውህደቱ የመድበለ ፓርቲን ያዳክማል የሚል እሳቤም እንደሌለው ተናግረዋል። የአማራ ዴሞክራሲያዊ ኃይሎች ንቅናቄ የታገለላቸው ሀሳቦች አዴፓም በአቋም እንደሚቀበላቸው አመልክተዋል፡፡
ስለሆነም ሁለቱ ድርጅቶች መዋሃዳቸው ለአንድ ዓላማ መቆማቸውን እንደሚያሳይ ያመለክታል ብለዋል፡፡ የአማራ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ እና የአማራ ዴሞክራሲያዊ ኃይሎች ንቅናቄ ውህደት ፈጥረው የጋራ መጠሪያቸው የአማራ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (አዴፓ) እንዲሆን መወሰኑን አቶ ምግባሩ አስረድተዋል፡፡ ውህደት የፈጠረው የአማራ ዴሞክራሲያዊ ኃይሎች ንቅናቄ የመረጃና ደህንነት ኃላፊ አቶ ፍፁም አየነው በበኩላቸው የአማራ ክልልን ህዝብ ጥያቄዎች ባግባቡ ለመመለስና ጠንካራ ክልላዊ ፓርቲ ለመመስረት ውህደቱ ወቅታዊ መሆኑን ገልፀዋል፡፡
ዓለምነው መኮንን
ነጋሽ መሐመድ
ሸዋዬ ለገሠ