1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የአዲስ ዓመት ክብረ በዓል በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል

ዓርብ፣ መስከረም 1 2013

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች የ2013 ዓ.ም አዲስ ዓመት አንድ አንድ አንዶች የኮቪድ 19 ወረርሽኝን ለመከላከል በሚደረገው ጥረት  ምክንያት በዓሉ በየቤቱ ተከብሮ ውሏል። በግጭት ምክክንያት የመተከል ዞን የተለያዩ ወረዳዎች ውስጥ ደግሞ በርካቶች በጊዜያዊ መጠለያ ጣቢያ ውስጥ በዓሉን ለማክበር ተገደዋል፡፡

https://p.dw.com/p/3iL5n
Asosa, West-Äthiopien und Hauptstadt der Region Benishangul-Gumuz
ምስል privat

የአዲስ ዓመት አከባበር በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል

በቤኒሻንጉል  ጉሙዝ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች የ2013 ዓ.ም አዲስ ዓመት አንድ አንድ አንዶች የኮቪድ 19 ወረርሽኝን ለመከላከል በሚደረገው ጥረት  ምክንያት በዓሉ በየቤቱ ተከብሮ ውሏል።  ከሐምሌ 2012 ዓ.ም መጨረሻ አንስቶ ግጭት ተፈጥሮ የነበሩባቸው የመተከል ዞን የተለያዩ ወረዳዎች ውስጥ ደግሞ በርካቶች በጊዜያዊ መጠለያ ጣቢያ ውስጥ በዓሉን ለማክበር ተገደዋል፡፡ በመተከል ዞን ጉባ ወረዳ ማንኩሽ ከተማ ውስጥ በመጠለያ ጣቢያ ያሉና ከሰሞኑ ደግሞ በዙኑ ወምበራና ቡሌን ወረዳዎች በተፈጠረው የጸጥታ ችግር ምክንያት ከ2ሺ በላይ ዜጎች አዲሱን ዓመት ከመኖሪያ ቀአቸው ውጭ አሳልፈዋል፡፡

ነጋሳ ደሳለኝ

ታምራት ዲንሳ

ሸዋዬ ለገሠ