1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የአዲስ አበባ ወቅታዊ ኹኔታ

ማክሰኞ፣ ኅዳር 21 2014

በኢትዮጵያ እና በሽብርተኝነት በተፈረጀው ሕወሓት መካከል ግልፅ ጦርነት ውስጥ ከተገባ 13ኛው ወራት ላይ እንገኛለን። የዲፕሎማሲ ማዕከል የሆነችው አዲስ አበባ መደበኛው የሕይወት ዑደት አልተስተጓጎለባትም።

https://p.dw.com/p/43feG
Äthiopien Addis Abeba
ምስል DW/S. Muchie

መደበኛው የሕይወት ዑደት አልተስተጓጎለባትም

በኢትዮጵያ እና በሽብርተኝነት በተፈረጀው ሕወሓት መካከል ግልፅ ጦርነት ውስጥ ከተገባ 13ኛው ወራት ላይ እንገኛለን። የዲፕሎማሲ ማዕከል የሆነችው አዲስ አበባ መደበኛው የሕይወት ዑደት አልተስተጓጎለባትም። ምዕራባዊያኑ ግን ዜጎቻቸው ከከተማዋ እንዲወጡ ውትወታቸውን አሁንም አላቆሙም። በከተማዋ ሕይወት ምን ይመስላል የየሚለውን በተወሰነ ደረጃ ለማየት ሞክረናል። የጦር ሠራዊቱን ግንባር ሆነው እየመሩ ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ዛሬ ባስተላለፉት መልዕክት የሕወሓት ታጣቂዎች መሣሪያ አውርደው እጃቸውን ለመከላከያ ሠራዊት እንዲሰጡና ሕይወታቸውን እንዲያተርፉ አሳስበዋል።

ሰለሞን ሙጬ

ማንተጋፍቶት ስለሺ

ነጋሽ መሐመድ