1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

«የአዲስ አበባ ባላደራ» መግለጫ

ዓርብ፣ መስከረም 30 2012

የአዲስ አበባ ባለ አደራ ምክር ቤት ጥቅምት 2 በአዲስ አበባ መስቀል አደባባይ ሰላማዊ ሰልፍ የጠራሁት ተስፋ የተጣለበት የዴሞክራሲያዊ ስርዓት ጅምር በመቀልበሱ ነው አለ።

https://p.dw.com/p/3R9ju
Äthiopien Addis Abeba Motorräder aus Stadt verbannt
ምስል DW/Solomon Musche

«ለሰልፉ የከተማው አስተዳደር አዎንታዊም አሉታዊም መልስ አልሰጠም»

ከዚህ በፊት በተለያየ መንገድ ነገሮች እንዲስተካከሉ ብንጮህም ሰሚ በማጣታችን ሁለተኛውን የሰላማዊ ትግል ስልት ለመጠቀም ተገደናል በዚህም መፍትሄ ካላከኘን በቀጣይ መንግሥትን ወደሚያስገድዱ የሥራ ማቆም እና ሌሎች የትግል ስልቶች ለመግባት እንገደዳለሁ ብሏል። በሕጉ መሠረት ሁሉንም መስፈርት አሟልቻለሁ ያለው ባለ አደራው ምክር ቤት ከከተማ መስተዳድሩ ግን እስካሁን በአዎንታም ሆነ በአሉታ ምላሽ አልተሰጠንም ያ ማለት ሰልፉን ፈቅዷል ማለት ነው ስለዚህም በሰልፉ ላይ አስፈላጊውን ጥበቃ የማድረግ ኃላፊነት እንዳለበትም አመልክቷል። ይህ መግለጫ በሚሰጥበት ወቅት የተወሰኑ ወጣቶች መግለጫውን በመቃወም ድምጻቸውን ሲያሰሙ ነበር። ሰሎሞን ሙጬ ዝርዝር ዘገባ ልኮልናል።

ሰሎሞን ሙጬ