እርዳታ ለጎንደር ተፈናቃዮች
ሐሙስ፣ የካቲት 14 2011ማስታወቂያ
ብሔራዊ የአደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን የአማራ ክልል ባቀረበው ጥያቄ መሰረት በማእከላዊ እና ምእራብ ጎንደር ዞኖች ለተፈናቀሉ 45 ሽህ 922 ዜጎች ካለፈው ሳምንት ጀምሮ ምግብ እና ምግብ ነክ ያልሆኑ የሰብአዊ ድጋፎችን መስጠት መጀመሩን አስታውቋል፡፡ ድጋፉ በየወሩ ይቀጥላል ያለው ኮሚሽኑ በመልሶ ማቋቋም ሥራዎች ላይም እንደሚሳተፍ ተናግሯል፡፡ ተፈናቃዮቹ ድጋፉ በቂ አይደልም እያሉ ቢሆንም ከክልሉ ባቀረበልን ጥያቄ መሠረት እያቀረብን ነው ሲሉ ኮሚሽኑ የህዝብ ግንኙነት እና ኮሙኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ ደበበ ዘውዴ ለ DW ተናግረዋል፡፡ ኢትዮጵያ በድርቅ፡ በጎርፍ ፡ በመሬት መንሸራተት እና መሰንጠቅ ዜጎቿን ከከፋ ጉዳት ለመታደግ እየሠራች ቢሆንም አሁን አሁን ደግሞ ግጭት ያስከተለው መፈናቀል ለሰብአዊ ድጋፍ የሚደረገውን ሥራ የበለጠ እንዲሰፋ አድርጎታል፡፡ የሚደረገውን ድጋፍ ፍትሃዊነት ለመከታተልም በመላሃገሪቱ 6 ቡድኖች ተሰማርተው አሰሳ እደረጉ መሆኑን ኮሚሽኑ ገልጿል፡፡ የአዲስ አበባው ወኪላችን ሰሎሞን ሙጬ ዝርዝር ዘገባ አለው ።
ሰሎሞን ሙጬ
ኂሩት መለሰ
ሸዋዬ ለገሠ