1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የአይሮፕላን አደጋ ሰለቦች አንደኛ ዓመት መታሰቢያ

ሰኞ፣ የካቲት 30 2012

ባለፈው አመት ቢሾፍቱ አቅራቢያ ጊምቢቾ ወረዳ ተከስክሶ ህይወታቸው ላለፈው የቦይንግ 737 - 8 ማክስ አውሮፕላን ተሳፋሪዎች ዛሬ በአካባቢው በሚኖሩ ሰዎች የአንድ አመት የሙት መታሰቢያ ስነ ስርአት ተከናወነላቸው።

https://p.dw.com/p/3Z3ny
Gedenkfeier für die Toten der abgestürzten Boing 737 -8 max Ethiopian Airlines
ምስል DW/S. Muchie

ለአይሮፕላን አደጋ ሟቾች የሙት ዓመት መታሰቢያ

ባለፈው አመት ቢሾፍቱ አቅራቢያ ጊምቢቾ ወረዳ ተከስክሶ ህይወታቸው ላለፈው የቦይንግ 737 - 8 ማክስ አውሮፕላን ተሳፋሪዎች ዛሬ በአካባቢው በሚኖሩ ሰዎች የ አንድ አመት የሙት መታሰቢያ ስነ ስርአት ተከናወነላቸው።
ከአዲስ አበባ ተነስቶ ወደ ኬንያ ሲበር የነበረውና የበረራ ቁጥሩ ET 302 የሆነው የኢትዮጵያ አየር መንገድ አውሮፕላን ውስጥ ተሳፍረው የነበሩት 157 ሰዎች ሙሉ በሙሉ የሞቱበት ቦታ ተከልሎና ታጥሮ ይገኛል። ዛሬ በተከናወነው የመታሰቢያ ስነ ሥርዓት ላይ በርከት ያሉ የአካባቢው ነዋሪዎች ተገኝተዋል።
አውሮፕላኑ የተከሰከሰበትን ቦታ አርሰን አንበላም በማለት ከቦይንግ ካሳ መውሰዳቸውን የሚናገሩት ነዋሪዎች ፣ ቦታው ቋሚ የተጎዱት ሰዎች መታሰቢያ እንዲሆን ትኩረት ሊሰጠው ይገባልም ብለዋል።

ሰለሞን ሙጬ

ልደት አበበ