የአየርላንድ ዲፕሎማቶች መባረር
ሐሙስ፣ ኅዳር 16 2014ማስታወቂያ
የኢትዮጵያ መንግስት በአዲስ አበባ የአየርላንድ ኤምባሲ ባልደረቦች የነበሩ አራት ዲፕሎማቶች በአንድ ሳምንት ጊዜ ውስጥ ኢትዮጵያን ለቅቀዉ እንዲወጡ ማሳወቁን የአየርላንድ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ትናንት አስታዉቋል።የአየር ላንድ ዉጪ ጉዳይ ሚንስቴር የኢትዮጵያ ዉሳኔ ጊዜያዊ ሊሆን እንደሚችልና ዲፕሎማቶቹ ተመልሰው ሥራቸውን እንደሚያከናውኑ ተስፋዉን ገልጧልም።የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ግን እስካሁን ስለዉሳኔ በይፋ ያለዉ ነገር የለም።
ሰለሞን ሙጬ
ነጋሽ መሐመድ
ሸዋዬ ለገሰ