1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የአውሮጳና የአፍሪቃ ኅብረት ሥልታዊ ትብብር

ማክሰኞ፣ ኅዳር 15 2013

ለአውሮጳ ኅብረት ይህ የአውሮጳውያን ዓመት የአፍርካ አመት እንዲሆን ነበር የታሰበው። ባለፈው ጥቅምት ወር የአውሮጳ ህብረት አባል አገሮችና የአፍርካ ህብረት መንግስታት መሪዎች ኢዚህ ብራስልስ ተገናኝተው አዲስ ያአፍርካና  አውሮጳ ኅብረት አጋርነት ስምምነት ሊያበስሩ ነበር ዕቅዱ።

https://p.dw.com/p/3llyU
Brüssel | Pressekonferenz zur EU-Afrika-Strategie mit Josep Borrell und Jutta Urpilainen
ምስል Getty Images/AFP/J. Thys

የአፍሪቃ አውሮጳ ሥልታዊ ትብብር

ለአውሮፓ ህብረት ይህ የአውሮፓውያን አመት የአፍርካ አመት እንዲሆን ነበር የታሰበው።  ባለፈው ጥቅምት ወር የአውሮፓ ህብረት አባል አገሮችና የአፍርካ ህብረት መንግስታት መሪዎች ኢዚህ ብራስልስ ተገናኝተው አዲስ ያአፍርካና  አውሮፓ ህብረት አጋርነት ስምምነት ሊያበስሩ ነበር ዕቅዱ። የአውሮፓ ህብረት ቀድሞ የህብረቱ አባል አገሮች ቅኝ ተገዥ ክነበሩት የአፍርካ፤ ካሪቢያን እና ፓስፊክ አገሮች ጋር አዲስ የንግድ ስምምነት የማድረግ ፍላጎትም ነበራቸው።  ይሁንና ምንም ያህል ውጤት ላይ ሳይደረስ አመቱ ሊያልቅ ነው፡፤ዛሬ የአውሮፓውያኑ አመት  አስራአንደኛው የህዳር ወር ላይ ነን።  በዚህም ምክኒያት አንዳንዶች አመቱን  የአውሮፓ ህብረትና አፍርካ ግንኙነትን በሚመለክት የባክነ ዓመት ይሉታል።   

አዲሱ የአውሮፓ ህብረት የውጭ ግኙነት ሀላፊ ሚስተር ጆሴፕ ቦሬል   ባለፈው መጋቢት ወር ወደ ስልጣን ሲመጡ የተለየ አመት መጀመሪያ ተደርጎ ነበር የተወሰደው። በጋዜጣዊ መግለጫቸው፤  አዲስ የአፍርካ ስትርቴጂ አዘጋጅተው  አቀረቡ፤ በሁለቱ አህጉሮች መካከል ጠንከራ ግንኙነትነ ለመመስረትም ቃል ገቡ 1 ድምጽ የአውሮፓ ህብረት በሁሉም  ማለት  በንግድ፤ ኢንቭስትሜንት፤ ልማት፤ ትብብርና ደህንነት፤ ከአፍሪካ ጋር ያለው ትብብር በአንደኛ ደረጃ የሚጠቀስ መሆኑን መዘንጋት አይገባም ። ይህ ሁለንተናዊ ግንኙነት እንዲቀጥል፤ እንዲያድግና የበለጠ ውጤማ እንዲሆን እንፈልጋለን በማለት አዲሱን እቅድቅቸውን አስታውቀው  ነበር።  

ይሁን እንጂ በሁለቱም ወገኖች በኩል ግንኙነትን እንደ አዲስ ለማሳደግ የነበረው ተነሳሽነት ብዙም አልነበረም። የአውሮፓ ህብረት መንግስታት አዲሱን የግንኑነት ስትራቴጂ  ገና ማጽደቅ ነበረባቸው፡፤  በዚህም ምክኒያት አዲሱ የአውሮፓ ህብረትና  አፍርካ አጋርነት ስምምነት ብስራት፤ ለሚቀጥለው አመት ሊተላልፈ ግድ ሁኗል ። ባለፈው ጥቅምት ወር ሊካሄድ የነበረው ከፍተኛ የአፍርካና ያውሮፓ ህብረት መሪዎች ጉባኤም ተሰርዟል።   ቬንትሮ የተባለው የጀርመን የልማት ድርጅት ምክትል ፕሬዝዳንት ሚስተር ማቲያስ ሞጌ  የዚህ ከፍተኛ ግምት የተሰጠው የሁለቱ አህጉሮች ግንኙነት ትኩረት ያላገኘበትን  ምክኒያት ሲያብራሩ፤ 2 ድምስ ። የአውሮፓ ህብረት በኮሮና ወረርሺኝ ብቻ ሳይሆን በሌሎችም የራሱ ጉዳዮች ተጠምዷል።

ብዙ ሚሊዮን ኢሮ የሚጠይቁ ወጭዎች አሉ። በመሆኑም በአሁኑ ወቅት ከፍርካ ጋር አዲስ የአጋርነት ስምምነት ማድረጉ ቅድሚያ የሚሰጠው አይደለም ብለዋል፤ ይህ ማለት ግን ወይዘሮ ሜርከል ፋላጎት አልነበራቸውም ማለት እንዳልሆነ በመግለጽ ጭምር።  ሆኖም ግን ችግሩ ከአውሮፓ ህብረት ብቻ ልነበረም ።  የአፍርካ ህብረት አገሮችም ለስምምነቱ መዘገግየት የራሳቸው አሉታዊ አስተዋጾ አለበት።  የኮሮና ወረርሺን አንዱ ምክኒያት ነው።  ይሁን እንጂ ለብዙዎቹ የአፍርካ አገሮች ከአውሮፓ ጋር የሚደረገው ግንኑነት ጠቀሜታም  ከዚህ በፊት የነበረውን ያህል አይደለም፡፤  ይህ የሆነበት ምክኒያትም እንደ ቻይና ያሉ ሌሎች የውጭ ሀይሎችም በመነሳታቸው ወይም በመምጣታቸው ነው። ጀርመናዊው  የኢኮኖሚ ባለሙያ  ሮበርት ካፔል በአፍሪካና ቻይና   ግንኙነ ላይ ባካሄዱት ጥናትና ባወጡት ጽሁፍ  ፤ ድምጽ ቻይና በአፍሪካ ያላትን ተሰሚነት አሳድጋለች።። ለጂኦ ፖልቲካም ይሁን ስትራቴጂካዊ ጥቅም ምክኒያት አውሮፓ ቻይና በአህጉሩ ያላትን ወታደራዊና ኢኮንሚያዊ ተሳትፎ ለመቋቋም የሚያስችል አጀንዳ ያስፈልጋታል በማለት አውሮፓ የአፍርካን ልባዊ አጋርነትና ወዳጅነትና ለማገኘት የበለጠ ጥረት ማድረግ እንዳለበት ያስገነዝባሉ።  

Brüssel | Pressekonferenz zur EU-Afrika-Strategie mit Josep Borrell
ምስል picture-alliance/Zuma/N. Landemard

ይህ ግን ቀላል እንዳልሆነ ነው የሚታመነው።  ብዙዎቹ የአፍርካ አገሮች ከአውሮፓ ጋር ባለቸው ግንኙነት ደስተኖች አይደሉም። ቬንቶ የተባለው የጀርመን የልማት ድርጅቶች ህብረት ያካሄደው ጥናት ያረጋገጠው ይህንን ነው፡፤ ድርጅቱ በአፍርክና አውሮፓ ካሉ  የሺቪል ድርጅቶች ተወካዮች ባሰባሰበው መረጀና ባካሄደው ጥናት፤ ካእፍርካ፤ ከግማሺ በላይ ከሆኑት የጥናቱ ተሳታፊዎች  ያገኘው መልስ የአፍርካና አውሮፓ ግንኑነት በጥሩ ሁኔታ እየሄደ እንዳልሆነ ወይም ጤናማ እንዳልሆነ የሚገልጽ ነው። በተጨማሪም ብዙዎቹ ግንኙነቱ ሊሻሻል ይችላል  ብለው የሚያስቡ አይድሉም እንደጥናቱ ውጤት ።: በጀርመን የአፍርካ ጥናት ማዕከል ተመራማሪ የሆኑት ናይጀራዊቷ ዶክተር ልይንዳ ኢሮሎም የአፍርካና አውሮፓ ግንኙነት ክመሰረቱ ችግር ያለበት ዕንደሆነ ነው የሚናገሩት፤ 3ድምስ የአፍርካና አውሮፓ ግንኑነት በእኩልነት ላይ የተመረተ ሆኖ አይውቅም፡ ።  አለማቀፋዊ ትብብር ይባላል ግን የአፍርካና አውሮፓ ግኙነት አሁንም የተዛባ ነው። አውሮፓ አዋቂ  አፍርካ ተማሪ የሆነበትም የባላይና የበታች ግንኙነት የሚንጸባረቅበት ነው።  

ለምሳሌ የንግዱን ግንኙነት ማየት ይችላል። አፍርካ የአውሮፓ ዋና አጋር ነው።  አፍርካ ወደ ውጭ ከሚልከው ጥሬ ዕቃ አንድ ሶስተኛው ወደ አውሮፓ ነው የሚላከው። ወደ ውስጥ ከሚያስገባው ሸቀጥም አንድ ሶስተኛው ከአውሮፓ ነው የሚገባው። ይሁን እንጂ ግንኙነታቸው  የእኩያሞች ግንኑነት ሆኖ አያውቅም።  አፍርካ በአብዛኛው  ወደ ወስጥ የሚያስገባው የእንዱስትሪ ውጤቶችን ሲሆን፤ ወደ ውጭ የሚልከው ደግሞ የማዕድን ጥሬ ዕቃዎችን እና የግብርና ውጤቶችን ነው። ይህ ደግሞ አፍርካ እንዱስትሪን እንዲያያስፋፋና  ስራ እንዲፈጥር አያስችለውም። እንደ ጀርመናዊው የኢኮኖሚ ባለሙያ ሮበርት ካፐል እምነት  ይኸ አይነቱ ግንኙነትም አፍርካ በአሁኑ ወቅት የተጋረጣበትን ችግር አይፈታም።   ከፍተኛ ቁጥር ያለው ስራ አጥ  ያለበትና ኢኮኖሚውም በአብዛናው ኢመደበኛ በመሆኑ አውሮፓ ይህንን ሁኔታ ለመቀየር ፋላጎት እንዲኖረው ያስፈልጋል ። 

የፍልሰተኖችና ስደተኖች ጉዳይ ሌላው የአውሮፓና አፍርካ ግንኑነ ትኩረት ነው፡፤  አውሮፓ በተለይ ከቅርብ አመታት ወዲህ የአፍርካ መንግስታት ወደ አውሮፓ በህገወጥ መንገድ የሚገቡትን ስደተኖች እንዲያስቆም ከፍተኛ ግፊት ሲያደርግ ቆይቷል። ይህን ለማድረግ የሚተባበሩ የአፍሪካ መንግስታትም የገንዘብና ቲክኒክ ድጋፍ ሲያገኙ ቆይተዋል። ከዚሁ ጋርም አውሮፓ በህጋዊ መንገድ ወደ አውሮፓ መግባት ለሚፈልጉ አፍርካውያን ሁኒታዎችን እንደሚያመቻች ቃል ተገብቶም ነበር። ይሁን እና ባለመያዎች እንደሚሉት ይህ የተገባ ቃል ተግባራዊ አልሆነም።ይልቁንም በአውሮፓ ለመስራትም ሆነ ለመማር ለሚፈልጉ አፍርካውያን ከሌሎቹ የበለጠ አስቸጋሪ እንደሆነ ነው የሚታመነው። ዶክተር ልይንዳ ኢሮሎ እንድሚሉት የአውሮፓ የስደተኖች ፓሊሲ የስፍርካ ስደተኖችን የሚያገል ነው፡  እንደእሳቸው እምነት ፖሊሲው የመዋቅርና የአተገባበር ችግሮች ያሉበት መሆኑን በብዙ ማሳያዎች ማረጋገጥ ይቻላል። እራሳቸው ኢመደበኛ፤ ህገወጥ፤ ፈላሲ የሚሉት ቃላት አሉታዊ ትርጉም የሚሰጡ ናቸው። 

Brüssel | Pressekonferenz zur EU-Afrika-Strategie mit Jutta Urpilainen
ምስል Getty Images/AFP/J. Thys

የዓውሮፓ ህብረት ያፍርካ ስትራቴጅ ሌሎች ጉድለቶች እንዳሉትም ነው የሚነገረው። ብራስልስ አምስት ከአፍርካ ጋር የሚተባበርባቸውን ዘርፎች ለይቷል፤ የአረንጓዴ ልማት፤ የዲጂታል ሽግግር  ዘላቂ ልማት ደህንነትና  የስደተች ጉዳይ። ነገር ግን ስትራቴጂው በተዘጋጀበት አግባብ ላይ ከሁለቱም ወገን ቅሬታ አለ።  ሚስተር ሞጌ እንደሚሉት  እንደዚህ አይነት ስትራቴጂ መዘጋጀት የነበርበት ከአፍርካ ህብረት ጋር በመመካከርና በጋራ ነበር ። እንደዚያ ቢሆን ለተግባራዊነቱ የበለጠ እድል የሚኖረው  ቢሆንም፤ የአሁኑ ግን አውሮፓ አዘጋጅቶ አፍርካ በስራ ላይ እንዲያውለው ያቀረበው ዓይነት ነው  

በመሆኑም የአውሮፓና አፍርካ አዲስ ግኙነትን በሚመለከት አሁን ሁሉም 2021ን ነው የሚጠብቀው።   በዙ የተጠበቀው የአፍሪክና አውሮፓ ህብረት አዲስ የአጋርነት ስትራቴጂ ስምምነ በሚቀጥለው አመት ይበሰራል ተብሎ ይጠበቃል።  ይሁን እንጂ የሁለቱ አህጉሮች ግንኙነት ጥልቅ ሊሆን እና ሊሰምርም የሚችለው የሁለቱ አህጉሮች መሪዎች በዕኩልነት ላይ የተመሰረተ ግንኙነት ለማድረግ  ሲስማሙና ሲተገብሩም እንደሆነ የሚታመን ሲሆን ፤ይህ የመሆኑ አለመሆኑ ሁኒታ ግን ወደፊት የሚታይ ነው የሚሆነው።  

ገበያው ንጉሴ/ዳንኤል ፔልስ

ማንተጋፍቶት ስለሺ