የአውሮጳ ኅብረትን ያሰጋዉ የኮሮና ተኅዋሲ
ማክሰኞ፣ የካቲት 17 2012ማስታወቂያ
የኮሮና ተሐዋሲ በአውሮጳም መስፋፋት መጀመሩ የአውሮጳ ኅብረትን እና አባል ሃገራትን እጅግ አሳስቧል። እስካሁን በጀርመን፤ ፈረንሳይ እና ብሪታንያ ተሐዋሲው ስለተገኘባቸው ጥቂት ሰዎች ከመነገሩ ባለፈ ስጋት ያልነበረው ይኽ ተሐዋሲ በአውሮጳ ስጋት ደቅኗል። በጣሊያን ካለፈው ዐርብ ወዲህ ብቻ 200 ሰዎች በተሐዋሲው መያዛቸው እና ስድስት ሰዎችም መሞታቸው በኅብረቱ ውስጥ ግዙፍ የጤና ቀውስ እንዳያስከትል አስግቷል። ጣልያን ውስጥ 11 ከተሞች ውስጥ ሰዎች እንዳይገቡም ኾነ ከከተማዪቱ እንዳይወጡ የሀገሪቱ መንግሥት ከልክሏል። የአውሮጳ ኮሚሽን የአስቸኳይ ጊዜ ርዳታ ኮሚሽን ኮሚሽነር እና የጤና እና ምግብ ኮሚሽነር ትናንት በጋራ መግለጫ ሰጥተዋል። የብራስልሱ ወኪላችን ተጨማሪ ዘገባ አለው።
ገበያው ንጉሤ
ማንተጋፍቶት ስለሺ
ነጋሽ መሐመድ