1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የአውሮጳ ኅብረት የሰብአዊ ጉዳዮች ልዑክ ኢትዮጵን ሊጎበኙ ነው

ማክሰኞ፣ ጥር 18 2013

በትግራይ ክልል ስላለው ሁኒታና በኢትዮጳያና ሱዳን የደንበር ውዝግብ ላይ ለሚኒስትሮቹ ማብራሪያ  ሰጥቻለሁ በማለት ሁኒታውን በቅርብ ለማየትና ከሚመለከታቸው አክላት ጋር ለመወይየትም  የፊንላንድ የውጭ ጉዳይ ሚኒስተር ሚስተር ፔካ ሀቪስት የአውሮጳ ህብረትን ከፍተኛ ልኡክ በመምራት በዚህ ወር መጨረሻ ወደ አካባቢው የሚሄዱ መሆኑን ቦሬል አስታውቀዋል።

https://p.dw.com/p/3oREw
Deutschland | Lateinamerika-Konferenz im Auswaertigen Amt in Berlin | Josep Borrell
ምስል Florian Gärtner/imago images/photothek

ስለ ኢትዮ-ሱዳን ድንበር ውዝግብም ማብራሪያ መሰጠቱ ተገልጧል

የአውሮፓ ኅብረት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች በጎርጎሪዮሱ አዲስ ዓመት 2021 የመጀመሪያቸው የሆነውን ስብሰባቸውን ሰኞ ጥር 17 ቀን፣ 2013 ዓ.ም፤ አካሂደዋል። በስብሰባው ከሩስያ የፖለቲካ ጉዳይ እስከ ኮቪድ ተሐዋሲ ስጋት ተነስቶ ውይይት ተካኺዶበታል። የኅብረቱ የውጭ ጉዳይ ኃላፊ ጆሴፕ ቦሬል፦ በአፍሪቃ ቀንድ ስላለው ኹኔታ ሚንሥትሮቹ መወያየታቸውን ገልጠዋል። ስለ ኢትዮጵያ ትግራይ ክልል እና የኢትዮጵያ ሱዳን ድንበር ውዝግብም ለሚንሥትሮቹ ማብራሪያ መስጠታቸውን ዐስታውቀዋል። ሁኔታውን በቅርብ ለማየትና ከሚመለከታቸው አክላት ጋር ለመወይየትም  የፊንላንድ የውጭ ጉዳይ ሚኒስተር ፔካ ሀቪስት የአውሮፓ ኅብረትን ከፍተኛ ልኡክ በመምራት በዚህ ወር መጨረሻ ወደ አካባቢው የሚሄዱ መሆኑን ተናግረዋል። የብራስልሱ ወኪላችን ገበያው ንጉሤ ተጨማሪ አለው።

የአውሮፓ ህብረት የውጭ  ጉዳይ ሚኒስትሮች  የአውሮጳውያን  አዲስ መት ከገባ ወዲህ የመጀመሪያ የሆነውን ስብሰባቸውን ትናንት አካሂደዋል። በህብረቱ የውጭ ጉዳይ ሀላፊ ሚስተር ጆሴፕ ቦሬየል የተመራው ይህ ስብሰባ ከተወያየባቸው አጀንዳዎች መካከል፣  ከአዲሱ የአሜሪካ አስተዳደር ጋር ስለሚኖረው ግንኙነት፣ የቱርክና አውሮፓ ህብረት ግንኑነት፣ የሩሲያው ተቃዋሚ  አሌክሲ ናቫልንይ እስር፣ የኮቪድ 19 ክትባት ክፍፍልና ስርጭትና እንዲሁም የአፍሪካ ቀንድ ሁኒታ የሚሉት ዋና ዋናዎቹ ነበሩ። 

በአዲሱ የባይደን አስተድደር የአሜሪካና  አውሮጳ ህብረት ግንኑነት ተሻሻሽሎ በአየር ለውጥና በሌሎች የሁለትዮሽና አለም አቀፍ ጉዳዮች ላይ አብረው ለመስራት ሚኒስትሮቹ ዝግጁ መሆናቸው በስብሰባው የተወሳ መሆኑ ታውቋል። እንዲሁም ከደረሰበት  የመመርዝ አደጋ በጀርመን ህክምና ሲያደርግ ቆይቶ ሲመለስ የታሰረውን የሩሲያ ተቃዋሚ መሪ ሚስተር ናቫልንይን በሚመለክት ሚስትሮቹ እስራቱን አውግዘው፣ የሩስያ መንግስት ሚስተር ናቫልኒን በአስቸኳይ እንዲፈታ ጠይቀዋል። በዚሁ ምክንያት በሩሲይ ላይ ማዕቀብ እዲጣል የጠየቁ የተወሰኑ አባል አገሮች ሚኒስትሮች የነበሩ ቢሆንም የማዕቀብ ውሳኔ ግን እንዳልተላለፈ ነው የተገለጸው።

 የአውሮፓ ኅብረት የውጭ ጉዳይ ኃላፊ ጆሴፕ ቦሬል
የአውሮፓ ኅብረት የውጭ ጉዳይ ኃላፊ ጆሴፕ ቦሬልምስል Olivier Hoslet/AFP/Getty Images

ሚኒስትሮቹ የኮቪድ  19 ክትባትን በሚመለከት፤ ምንም እንኳ በአሁኑ ወቅት  ለአውሮጳ አገሮችም የክትባት ምርትና ስርጭት ችግር ያለበት ቢሆንም፣ ወረርሺኙንን የመከላከሉ ስራ ሊሳካ የሚችለው ግን  ክትባቱ በሁሉም አገሮች ሲሰጥ መሆኑንን በማመን አገሮች ሌሎችን የመርዳትና የመተባበር ሀላፊነት ያለባቸው መሆኑን ሚኒስትሮቹ እንደተረዱት ሚስተር ቦሩኤል በጋዘጣዊ መግለጫቸው አስታውቀዋል።

የወጭ ጉዳይ ሀላፊው ሚስተር ቦሬየል በአፍርካ ቀንድ ስላለው ሁኒታም ሚኒስትሮቹ የተወያዩ መሆኑን አስታውቀዋል ። የአፍርካ ቀንድን ሁኔታ በጥልቀት አይተናል። በአካባቢው ሌላ ተጨማሪ አለመረጋጋት እንዳይፈጠር ጥረት ማድረግ የሚያስፈልግ መሆኑንም ተገንዝበናል።  በኢትዮጵያ የትግራይ ክልል ስላለው ሁኒታና በኢትዮጳያና ሱዳን የደንበር ውዝግብ ላይ ለሚኒስትሮቹ ማብራሪያ  ሰጥቻለሁ በማለት ሁኒታውን በቅርብ ለማየትና ከሚመለከታቸው አክላት ጋር ለመወይየትም  የፊንላንድ የውጭ ጉዳይ ሚኒስተር ሚስተር ፔካ ሀቪስት የአውሮፓ ህብረትን ከፍተኛ ልኡክ በመምራት በዚህ ወር መጨረሻ ወደ አካባቢው የሚሄዱ መሆኑን አስታውቀዋል።

የአውሮፓ ህብረት፣ የኢትዮጵያ መንግስት በትግራይ ክልል  አካሄድኩት በሚለው ህግ የማስከበር ዘመቻ፣ በሰላማዊ ሰዎች ላይ የሚደርሱ ጉዳቶችና የሰብዊ መብት ጥሰቶች የሚያሳስቡት መሆኑን በመግለጽ  ተደጋጋሚ መገለጫዎችን ማውጣቱ ይታወሳል። የእርዳታ ሰጭ ድርጅቶች በትግራይ ክልል ገብተው የርዳታ ስራቸውን በነጻ እንዲያከናዉኑ  እንዲፈቀድላቸው፣ ጋዜጠኖችና የሰባዊ መብት ድርጅቶቸ ወደ ክልሉ ገበተው ያለውን ሁኔታ እንዲያዩና እንዲዘግቡ በአጠቃላይም በክልል የህግ የበላይነት እንዲከበርና የዜጎች መብት እንዲጠበቅ በመጠየቅ፣ ይህ መሆኑ እስከሚረጋገጥ ድረስም ለዚህ ወቅት የሚሰጠውን 90 ሚሊዮን ኢሮ የበጀት ድጎማ የሚያዘገይ መሆኑን ማስታወቁ አይዘነጋም።

EU Flagge
ምስል picture-alliance/NurPhoto/N. Economou

የኢትዮጵያ መንግስት ግን የሚቀርብበትን ክስና ውንጀላ ሲያስተባብል የቆየ ሲሆን፣ በተለይ በአሁኑ ወቅት የዕርዳታ ድርጅቶች ወደ ክልሉ ገብተው የተራዶ ስራቸውን በነጻ እያከናወኑ  እንደሆነ እየገለጸ ነው። በቅርቡ ወደ ኢትዮጵያ ይዘልቃል የተባለው በፊንላድ የውጭ ጉዳይ ሚኒስተር ሚስተር ፔካ ሀቪስት የሚመራው የህብረቱ ከፍተኛ ልኡክ፣ ሁኒታዎችን በቅርበት በማየትና  ከከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣኖች፣ ከሰባዊ መብትና እርዳታ ሰጭ ድርጅቶች ጋር በመያየትና ምናልባትም አካባቢውን በመጎብኘት  ህብረቱ በኢትዮጵያ ላይ በቀጣይ ለሚወሰደው እርምጃ የሚረዱ ግባቶችን ይዞ ይመለሳል ተብሎ ይጠበቃል።።
ገበያው ንጉሴ
ማንተጋፍቶት ስለሺ 

አዜብ ታደሰ