የአውሮጳ ኅብረት እና የጀርመን መንግሥት ድጋፍ በኢትዮጵያ
ዓርብ፣ ሰኔ 14 2011ማስታወቂያ
የአውሮጳ ኅብረት እና የጀርመን መንግሥት በኢትዮጵያ በግብርናው ዘርፍ ያደረጉት የድጋፍ እና የትብብር ውጤት አመርቂ ኾኖ በመገኘቱ ድጋፉ ለመጪዎቹ ሦስት ዓመታት የሚቀጥል መኾኑ ተገለጠ። ባለፉት ሦስት ዓመታት ከ30 ሚሊዮን ዩሮ በላይ ለዘርፉ ተመድቦ እንደነበርም ተገልጧል። ርዳታውንም ከመንግሥት ጋር በመተባበር ተግባራዊ ሲያደርግ የቆየው የጀርመን አጋርነት ለዓለም አቀፍ ትብብር (GIZ) የተሰኘው የቴክኒክ ተራድኦ ድርጅት ድጋፉን እንደሚቀጥል ተናግሯል። ጌታቸው ተድላ ኃይለ-ጊዮርጊስ ዝርዝር ዘገባውን ከአዲስ አበባ ልኮልናል።
ጌታቸው ተድላ ኃይለ-ጊዮርጊስ
ማንተጋፍቶት ስለሺ
እሸቴ በቀለ