1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የአውሮጳ ኅብረት ስለ ትግራይ ክልል የአየር ጥቃቱ

ሐሙስ፣ ሰኔ 17 2013

የአውሮጳ ኅብረቱ ትግራይ ክልል ውስጥ የገበያ ቦታ ከአየር ተደበደበ መባሉን አወገዘ። የኢትዮጵያ መከላከያ ገበያ ተደበደበ መባሉ የተሳሳተ መረጃ እንደሆነ በመጥቀስ በዐየር ጥቃቱ ብርቱ ጉዳት የደረሰበት የሕወሓት ታማኝ ታጣቂ ቡድን መሆኑን ዐሳውቋል።

https://p.dw.com/p/3vVzI
Russland Treffen Borell - Lawrow
ምስል Russian Foreign Ministry/REUTERS

ሚስተር ባላዝስ ኢጅቫሪን ተጠይቀዋል

የአውሮጳ ኅብረት በኢትዮጵያ የትግራይ ክልል  በአንድ ቀበሌ የገበያ ቦታ  የቦምብ ጥቃት መፈጸሙን የሚገልጽ ዘገባ እንደደረሰው በመግለጽ  ድርጊቱን አውግዟል። በሕብረቱ የውጭ ጉዳይ ኃላፊ ሚስተር ጆሰፍ ቦሪየልና ያደጋ መከላከያ ኮሚሽን ኮሚሽነር ሚስተር ጀኔዝ ሌናርሲክ ዛሬ በጋራ ባወጡት መግለጫ፤ ባለፈው ማክሰኞ በደጋ ተንቤን ቶጎጋ አካባቢ በእዳጋ ሰሉስ ቀበሌ የቦምብ ጥቃት መፍረጸሙን የደረሳቸው ዘገባዎች ያረጋገጡላቸው መሆኑን በመጥቀስ ነው ድርጊቱን ያወገዙት። ይህ ድርጊት ሌላ የሰባዊና ዓለማቀፍ ሕግጋት የሚጥስ ድርጊት መሆኑን በመግለጽም የአውሮፓ ህብረት የሰላምዊ ሰዎችን ዒላማ የሚያደርጉ ጥቃቶችን በጽኑ የሚያወግዝ መሆኑን ባለስልጣኖቹ በጋራ መገልጫቸው ዐስታውቀዋል።

የኢትዮጵይ መንግሥት፤ የመከላከያ ሠራዊቱ በሰላማዊ ሰዎች ላይ ጥቃት እንደማይፈጽም በመግለጽ፤ በገበያ ላይ የተፈጸመ የአየር ድብደባ የለም ሲል ተሰምቷል። የህብረቱን ቃል ዓቀባይ ሚስተር ባላዝስ ኢጅቫሪንን  ጥቃት መፈጸሙን የሚገልጹት መረጃዎችን አስተማማኘትና  ስለህብረቱ መግለጫ ይዘት፤ እንዲሁም በቀጣይ ህብረቱ ሊወስዳቸው ስለሚቺሉት እርምጃዎች  በስልክ ጠይቄያቸው ነበር። ቃል አቀባዩም፤ በቅድሚያ ስሁኒታው ላይ የሚሰጡት መልሶች በአካባቢው ያለውን ሁኒታና  ላለፉት ስምንት ወራትም ጦርነት ሲካሄድ የቆየ መሆኑን ከግምት ውስጥ በማስገባት መሆኑን በመግለጽ ባለፈው ማክሰኞ ተፍጽሟል ያሉትን አብራርተዋል። ድምጽ ትናንት የተፈጸመው ጥቃት በፍጹም ተገቢነት የለውም። በተለይ  የቆሰሉና የተጎዱትን  ለመርዳት ወደ አካባቢው የሚሄዱ የህክምና ባለሙያዎች ታግድዋል መባሉ ከተረጋገጠ ትልቅ  ወንጀል ነው በማለት  እንደዚህ አይነት ድርጊቶች የጄነቫን ድንጋጌና እአለማቀፍ ህግን የሚጥሱ ናቸው፤ የአውሮፓ ህብረትም ስልተፈጸመው ጥቃት ነጻ ምርመራ እንዲደረግ ይጠይቃል ይጠብቃልም ብለዋል።

ህብረቱ ከዚህ መግለጫው በኋላ በቀጣይ የሚወስደው እርምጃ ምን ሊሆን ይችላል በማለት ለቀረበላቸው ጥያቄ ሲመልሱም፤ የውሮፓ ህብረት ግጭቱ ከተቀሰቀሰበት ወቅት  ጀምሮ በፖለቲካና  በሰባዊ እርድታ በስፋት ሲሳተፍ መቆየቱን ጠቅሰው፤  እስክሁን የ50 ሚሊዮን ዩሮ የሰባዊ ርዳታ መለገሱን አስታውሰዋል። በቀጣይ ህብረቱ ሊያደርግና ሊወስድ የሚችለውን ሲገልጹም፤ድምጽ በቀጣይ የሚሆነው በካባቢው ላይ ውይይት ማድረግ ነው። የህብረቱ የውጭ ጉዳይ ሃላፊ ሚስተር ቦሪየል  በሚቀጥለው የሀምሌ ወር በሚደረገው የህብረቱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ስብሰባ የኢትዮጵያ በተለይም በትግራይ ክልል ያለው ሁኒታ በአጀንዳ እንዲያዝ አድረገውዋል በማለት ይህም አባል አገሮች ተጨማሪ እርምጃዎችን ለመውሰድ እድል ሊሰጣቸው እንደሚችል ያላቸውን እምነት ዐስታውቀዋል።

በተመሳስይ፤ ይህን ማክሰኖ እለት በገበያ ቦታ ደረሰ የተባለውን የአየር ድብደባና በተለይም የጤና ባለሙያዎች ጉዳት የደረሰባቸውን ሰዎች ለመርዳት ወደ ቦታው እንዳገቡ የተከለከሉበትን ሁኒታ የአሜርካው ስቴት ዲፓርትሜትንም ያወገዘው መሆኑ ታውቋል።

ገበያው ንጉሤ
ማንተጋፍቶት ስለሺ
ኂሩት መለሰ