1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የአውሮጳ ኅብረት መሪዎች ጉባኤ በብራስልስ

ዓርብ፣ መጋቢት 15 2015

ቤልጂየም ብራስል ውስጥ ለሁለት ቀናት በዘቀው የአውሮጳ ኅብረት የመሪዎች ጉባኤ አባል ሃገራቱ ኢኮኖሚና የኑሮ ውድነት፤ የስደተኞች ጉዳይና የውጭ ግንኙነት እንዲሁም የዩክሬን ጉዳይ ላይ ተወያይተው ውሳኔ አሳልፈዋል ። ኅብረቱ ዩክሬን የሩስያ ጦርን እንድትመክት በአንድ ዓመት 1 ሚሊዮን የመድፍ ጥይቶችን ለማቀበል መስማማቱን ትናንት ይፋ አድርጓል ።

https://p.dw.com/p/4PBjj
Belgien EU Gipfel Italien Frankreich Macron Meloni
ምስል Petr Kupec/CTK Photo/imago images

የዩክሬን ፕሬዚደንት የጦር ጄቶችም በአፋጣኝ እንዲላክላቸው ጠይቀዋል

ቤልጂየም ብራስል ውስጥ ለሁለት ቀናት በዘቀው የአውሮጳ ኅብረት የመሪዎች ጉባኤ አባል ሃገራቱ ኢኮኖሚና የኑሮ ውድነት፤ የስደተኞች ጉዳይና የውጭ ግንኙነት እንዲሁም የዩክሬን ጉዳይ ላይ ተወያይተው ውሳኔ አሳልፈዋል ። የአውሮጳ ኅብረት አባል አገራት መሪዎች ዩክሬን የሩስያ ጦርን እንድትመክት በአንድ ዓመት 1 ሚሊዮን የመድፍ ጥይቶችን ለማቀበል መስማማታቸውንም ትናንት ይፋ አድርገዋል ። የዩክሬን ፕሬዚደንት ቮሎዶሚር ዜሌንስኪ የአውሮጳ አባል ሃገራት ታንኮች እና የጦር ጄቶችም በአስቸኳይ  እንዲሰጧቸው ጠይቀዋል ። ሃያ ሰባቱ አባል ሃገራት በግል የራሳቸውን ውሳኔ ማስተላለፍ ይችላሉ ተብሏል ። ፖላንድ እና ስሎቫኪያ ለዩክሬን የጦር ጄቶችን ለመስጠት ቀደም ሲል ውሳኔ አሳልፈዋል ። የአውሮጳ ኅብረት ለዩክሬን የዚህን ያህል መጠን የጦር መሣሪያ ድጋፍ ማድረጉ ኅብረቱ ከሚመራባቸው መርኆች ጋር አይጣረስም ወይ? የሚል ጥያቄም ተነስቶ ነበር ። 

የ27ቱ የአውሮጳ ኅብረት መሪዎች ሁለት ቀን የዘለቀ ስብሰባ ቤልጂየም ብራስልስ ከተማ ውስጥ አካሂደው በህብረቱ ኢኮኖሚና የኑሮ ውድነት ላይ፤ የስደተኞች ጉዳይና የውጭ ግንኙነት አጀንዳዎች በሰፈው ተወያይተው ውሳኔዎችን አስልፈዋል ። የዩክሬኑ ፕሬዝድንት ሚስተር ቮሌድሜር ዘለነስኪ የህብረቱ መሪዎች ተዋጊ አውሮፕላኖች ጨምሮ የጦር መሳሪያዎችን ባስቸኳይ እንድሊኩላቸው በቪዲዮ መልክት ያስተላለፉ ሲሆን፤ የመንግስታቱ ድርጅት ዋና ጸሐፊ አንቶኒዮ ጉቴሬሽ ደግሞ በአካል ተገንተው ከመሪዎቹ ጋር በተለይ በምግብ ዋስትናና የአየር ንብረት አጀንዳዎች ላይ መወያየታቸው ታውቋል።

የዩክሬን ወታደሮች በጦር አውድ መድፎችን ለተኩስ ሲያዘጋጁ፦ ፎቶ ከክምችት ማኅደር
የዩክሬን ወታደሮች በጦር አውድ መድፎችን ለተኩስ ሲያዘጋጁ፦ ፎቶ ከክምችት ማኅደርምስል Sergey Shestak/AFP

በስድስት ሳምንታት ውስጥ ዳግም የተካሄደው ይህ የህብረቱ መሪዎች ጉባኤ፤ የዩክሬኑ ጦርነት ግለት በጨመረበት፤ ከጦርነቱ ጋር በተያያዘና በሌሎችም ምክኒያቶች በሁሉም የህብረቱ አገሮች በተክስተው የኢኮኖሚ ችግርና የኑሮ ውድነት ምክኒያት የተቃውሞ ድሞሶች እየተሰሙ ባለበት ወቅት፤ የፋይናንስ ቀውስ እንዳይከሰትም ስጋት ባጫረበት ግዜ፤ እንዲሁም ከሁለት ቀናት በፊት የቻይናው መሪ ሚስተር ጂፒንግ በሞስኮ ተገኝተው አገራቸው በምራባውያን ማዕቀብ ውስጥ ካለችው ሩሲያ ጋር ያላትን ግንኑነት አጠናክራ እንደምትቀጥል በገለጹበት ወቅት የተካሄደ በመሆኑ የተለየ ተደርጎ ተወስዷል።

የአውሮጳ ምክር ቤት ፕሬዝዳንትና የሰብሰብው መሪ ቻርለስ ሚሸል ስብሰብው የተክሄደበትን ድባብ፤ «ባንድ ጊዜ በርካታ ችግሮች ናቸው ያጋጠሙን፣ የጦርነቱ መዘዝና ያስከተላቸው ችግሮች፣ የሀይል አቅርቦት እጥረትና ቀውስ፤ የአየር ንብረት ለውጥ ሽግግር፣ የዲጂታል ሽግግር ችግር» የመሳሰሉት ያንዣበበት መሆኑን ገልሰዋል። 

መሪዎቹ ዛሬም ለዩክሬን ያላቸውን ድጋፍ በመግለጽም የሚሰጡትን የገንዘብና የጦር መሳሪያ ርዳታ እንደሚቀጥሉ በማረጋገጥ በሚቀጥሉት 12 ወራት ውስጥ የመድፍ ተተኳሽ ብቻ አንድ ሚሊዮን ያህል ለመላክ የተስማሙ መሆኑ ተገልጿል። ፕሬዝዳንት ዘለንስኪ አሁን ጥያቄያቸው በተለይ በተዋጊ ጀቶች ላይ እንዳተኮረ የሚታወቅ ሲሆን፤ እስካሁን ፖላንድና ስሎቫኪያ ሚግ ተዋጊ ጀቶችን ለመላክ እንደወሰኑ ታውቋል። ሌሎች አገሮችና ህብረቱ ባጠቃላይ ዘመናዊ ተዋጊ ጀቶችን ለዩክሬን ያቀርብ እንደሆን የተጠየቁት የስብሰብው መሪ ሚስተር ሚሸል፤ «እንደዚህ ዓይነቶቹ ውሳኔዎች በራሳቸው ባባል አገሮቹ የሚወሰኑ ናቸው።  ባጠቃላይ ግን ዩክሬን ብዙ ድጋፍና የጦር መስሪያ እርዳታ የሚያስፈልጋት መሆኑ ግልጽ ነው» ሲሉ አባል መንግስታት በየግላቸው ርምጃዎችን ሊወስዱ እንድሚችሉ ጠቁመዋል ። የአውሮጳ ኅብረት ለዩክሬን የዚህን ያህል መጠን የጦር መሳሪያ ድጋፍ ማድረጉ ህብረቱ ከሚመራባቸው መርሆች ጋር አይጣረስም ወይ? ተብለው የተጠየቁት ሚስተር ሚሸል፤ ዩክሬንን የምንደግፈው ግዛታዊ አንድነቷን እንድታስከብርና ሉኡላዊነቷን ኧንድታሰጠብቅ እንጂ ሩሲያን ለመውጋት አይይደለም ሲሉ ተከራክረዋል፤ «እኛ ዩክሬንን በመርዳት የዴሞክራሲ መርሆችንና እሴቶችን ነው የምናስከብረው። ለዓለም ሕግ መከበርም ነው የምንታገለው። ዛሬ ዩኪሬንን አለመርዳት ወደፊት ዓለም ሰላም እንዳይሆን መፍቀድ ነው የሚሆነው በማለት ለዩኪሬን የሚስጠው ማናቸውም ድጋፍ ለሰላምና ዴሞክራሲ የሚደረግ ድጋፍ እንደሆነ ገልጸዋል።

የዩክሬን ወታደሮች በጦር አውድ የተኮሷቸው የመድፍ አረሮች እሳት ሲተፉ ፦ ፎቶ ከክምችት ማኅደር
የዩክሬን ወታደሮች በጦር አውድ የተኮሷቸው የመድፍ አረሮች እሳት ሲተፉ ፦ ፎቶ ከክምችት ማኅደርምስል Sergey Shestak/AFP

ይሁን እንጂ የጦር መሳሪያ በመላክ ስላም መፍጠር አይቻልም በማለት መንግስታት የጦር መሳሪያን መላክ አቁመው የሰላም አማራጮችን እንዲፈልጉና በዚህም ዩክሬንን ከመፍረስ ሕዝቦቿን ከዕልቂት እንዲታደጉ የሚጠይቁ ድምፆችም መሰማት ጀምረዋል። 

ገበያው ንጉሤ

ማንተጋፍቶት ስለሺ

እሸቴ በቀለ