1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የአውሮጳ ሕብረትና የኢትዮጵያ መንግሥት የመረጃ ልዩነት

ዓርብ፣ የካቲት 19 2013

የአውሮጳ ሕብረት የውጭ ግንኙነት ኃላፊ ጆሴፍ ቦሬል ወደ አካባቢው በላኩት ቡድን ዘገባ መሠረት በማድረግ 80 ከመቶ የሚሆነው የትግራይ ሕዝብ ርዳታ እየደረሰው አይደለም ብለዋል። የኢትዮጵያ መንግሥት በበኩሉ ከበርካታ የርዳታ ድርጅቶች ጋር በመተባበር ከሞላ ጎደል በሁሉም የትግራይ አካባቢዎች በሚባል ደረጃ ርዳታውን እያከፋፈለ መሆኑን እየገለፀ ነው።

https://p.dw.com/p/3pyhm
EU Flagge
ምስል picture-alliance/NurPhoto/N. Economou

«የተንታኝ ማብራሪያና ምክረ ሃሳብ»

የኢትዮጵያ መንግሥት ከሦስት ወራት በፊት በትግራይ ክልል ሕግ ማስከበር የሚለውን ርምጃ መውሰድ ከጀመረ ወዲህ ከበርካታ መንግሥታት ሰብኦዊና የእርዳታ ድርጅቶች ከፍተኛ ወቀሳና ትችት ይቀርብበታል። በዋናነትም በሰላማዊ ሰዎችና ሴቶች ላይ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች እየተፈጸሙ ነው ለተፈናቀሉና ርዳታ ለሚሹ ሰዎች በነጻነት ርዳታ ማድረስ አልቻለም የሚሉ ይጠቀሳሉ። የአውሮጳ ህብረት የውጭ ግንኙነት ኃላፊ ጆሴፍ ቦሬል ወደ አካባቢው ልከውት የነበረውን ቡድን ዘገባ መሠረት በማድረግ 80 ከመቶ የሚሆነው የትግራይ ሕዝብ ርዳታ እየደረሰው አይደለም ብለዋል። የኢትዮጵያ መንግሥት በበኩሉ ከበርካታ የርዳታ ድርጅቶች ጋር በመተባበር ከሞላ ጎደል በሁሉም የትግራይ አካባቢዎች በሚባል ደረጃ ርዳታውን እያከፋፈለ መሆኑን እየገለፀ ነው። የመረጃ ልዩነቱ ከየት መጣ?

ገበያው ንጉሤ 

ሸዋዬ ለገሠ

ኂሩት መለሰ