የአውሮጳ ሕብረት የመሪዎች ጉባኤ ፍጻሜ
ማክሰኞ፣ ጥቅምት 11 2012ማስታወቂያ
ትናንት እና ዛሬ ብራሰልስ ቤልጅየም ውስጥ የተካሄደው የአውሮጳ ሕብረት አባል ሃገራት መሪዎች ጉባኤ ወሳኝ በሆኑ የተለያዩ ጉዳዮች ላይ ተነጋግሮ ውሳኔዎችን አሳልፏል። ጉባኤው ትኩረት ሰጥቶ የተነጋገረበትን አዲሱን የብሬግዚት ውል አጽድቋል። ሕብረቱ እና ብሪታንያ ትናንት የተስማሙበትን ውል ተግባራዊ ሊሆን የሚችለው ግን የብሪታንያ ፓርላማ እንደ ቀደመው ውል ውድቅ ካላደረገው ነው። ቱርክ በሶሪያ የምታካሂደውን ወታደራዊ ዘመቻ እንድታቆምም ጉባኤው ጠይቋል። ለቱርክ የጦር መሳሪያ ላለመሸጥም ተስማምቷል። የብራሰልሱ ዘጋቢያችን ዝርዝሩን ልኮልናል።
ገበያው ንጉሴ
ኂሩት መለሰ
ሸዋዬ ለገሠ