የአውሮጳ ሕብረት ባለሥልጣናት ምርጫ
ረቡዕ፣ ሰኔ 26 2011ማስታወቂያ
ለሕብረቱ ፓርላማ ሊቀመንበርነት የጣሊያኑ የምክር ቤቱ አባል ሶሻል ዴሞክራቱ ዴቪድ ማሪያ ሳሶሊኒ 345 ድምፅ አግኝተው የተመረጡ ሲሆን፤ ፈረንሳዊቱ የዓለም አቀፉ የገንዘብ ተቋም ኃላፊ ክርስቲን ላጋርድ ደግሞ የአውሮጳ ማዕከላዊ ባንክ ፕሬዝደንት ሆነዋል። የሕብረቱ መሪዎች በተለመደው መንገድ በአጭር ጊዜ ውስጥ የሕብረቱን ትላልቅ የኃላፊነት ቦታዎች የሚይዙ ባለሥልጣናትን በመምረጡ ከመግባባት ከመግባባት ለመድረስ ጊዜ ፈጅተዋል። ለዚህም አንድም ባለፈው ግንቦት የተካሄደው ምርጫ ያስከተለው ያልተጠበቀ ውጤት፤ አንድም ሃገራት በተናጠልም ሆነ በአካባቢ ይገባናል የሚሉትን ጥቅም ለማስጠበቅ የነበረው ፉክክር በምክንያትነት ይጠቀሳል። ገበያው ንጉሤ ከብራስልስ ዝርዝር ዘገባ ልኮልናል።
ገበያው ንጉሤ
ሸዋዬ ለገሠ
ኂሩት መለሰ