1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የአውሮጳ ህብረትና ጃፓን የጋራ ጉባኤ

ሐሙስ፣ ግንቦት 4 2014

ሁለቱ ወገኖች በጉባያቸው ማጠቃለያ ባወጡት የጋር መግለጫም፤ ሩሲያ ነጻና ሉላዊት አገር በሆነችው ዩክሬን ላይ የፈጸመችው ህገወጥ ወረራ፤ የዓለማቀፍ ህግንና የመንግስታቱ ድርጅትን መርሆዎች የሚጥስ፤ የአውሮጳንና የአለምን ሰላምም አደጋ ላይ የሚጥል ነው በማለት አጥብቀው ኮንነውታል።

https://p.dw.com/p/4BCyz
Japan | Gipfeltreffen zwischen der EU und Japan
ምስል kyodo/dpa/picture alliance

የአውሮጳ ህብረትና ጃፓን የጋራ ጉባኤ

የአውሮፓ ህብረትና ጃፓን 28ኛው የጋራ ጉባኤ ዛሬ በቶኪዮ ተካሂዷል። ህብረቱን ወክለው በጉባኤው የተገኙት የካውንስሉ ፕሬዝድንት ሚስተር ቻርለስ ሚሸልና የኮሚሺኑ ፕሬዝዳንት ወይዘሮ ፎንዴር ሌየን ናቸው። አስተናጋጁ የጃፓን ጠቅላይ ሚኒስተር ሚስተር ፉሚዮ ኪሺዳ  የመሩት ይህ ጉባኤ፤ በሁለትዮሽ የንግድ፣ የደህንነትና የአየር ንብረት ለውጥ አጀንዳዎች ተወያይቶ ውሳኔዎችን እንዳሳለፈ ቢታወቅም፤ የዩክሬን ጦርነትና ቻይና በካባቢውና አለማቀፍ ግንኑነት ላይ የምታራምደው አቋም ዋናዎቹና ጉባኤው በጥልቀት የተወያዩባቸው አጀንዳዎች ነበሩ ተብሏል;። 
ሁለቱም የህብረቱ ከፍተኛ ባለስልጣኖች፤ ከጃፓን መሪዎች ጋር ባደረጉዋቸው ውይይቶችም ሆነ በጋራ በሰጡዋቸው መግለጫዎች፤ በአሁኑ ወቅት ሩሲያ ስጋት የሆነቸው ለዩክሬን ወይም ለአውሮፓ ብቻ ሳይሆን ለአለም ሰላም ጭምር ነው የሚለውን አቋማቸውን አንጸባርቀዋል። የአውሮፓ ህብረትና ጃፓን የጋራ የዴሞክራሲና የኢኮኖሚ ሞዴሎችን የሚያራምዱ፤ ተመሳሳይ ራዕይ ያላቸው፤ በህግና ህግ  ብቻ ጥቅሞቻቸውን የሚያራምዱ፤ በአሳታፊ (መልቲላቴራሊዝም) አለማቀፍ ስራት የሚይምኑ መሆናቸውን ገልጸው፤ በአሁኑ ወቅት ግን ይህ አሰራር ፈተና ውስጥ የገባ በመሆኑ የአውሮፓ ህብረት እንደ ጃፓን ከመሰሉ ተመሳሳይ እምነት ካላቸው አገሮች ጋር ትብብሩን ማጠናከር እንዳለበት እንደሚያምንና ይህ 28ኛው ጉበኤም በዚህ መንፈስ የተከሄደ እንደሆነ ገልጸዋል።

EU - Japan Gipfel
ምስል Dursun Aydemir/AA/picture alliance

የካውንስሉ ፕሬዝዳንት ሚስተር ሚሸልም ይህ የ28ኝው ጉባኤ የተካሄደበት አውድ ልዩ መሆኑን ነው በመግለጫው የተናገሩት: “ሩሲያ በዩክሬን ላይ የከፈተችው ጦርነት፤  የጠበቀ ግንኑንትና ትብብር መፍጠርን ቅንጦት ሳይሆን አስፈላጊ እንዲሆን አድርጎታል። የዛሬው  ጉባኤም በዚህ መንፈስ የተክሄደና በሁሉም ዘርፎች የማንደርገውን ትብብር አጠናክሮ ለማስቀጠል  የሚረዳ ነው” ብለዋል። ፕሬዝዳንት ሚሸል በሩሲያ ላይ የተጣሉ ማዕቀቦች ሙሉ በሙሉ ተግባራዊ በሚሆኑበትና እንዳይጣሱም ለማድረግ በሚያስችሉ አሰራሮች ላይም እንደተወያዩ፤ እንዲሁም የጦር ወንጀለኞች ለፍርድ እንዲቀርቡና ጦርነቱ በአለማቀፍ የሀይል አቅርቦት ላይ ስለሚኖረው ተጽኖም በጥልቀት የተወያዩ መሆኑን አስታውቀዋል። 


 የኮሚሽኑፕሬዝዳንት ወይዘሮ ኡርዙላ ፎንዴርላየንም በመግለጫቸው፤ የዓለም  ስጋት ናት ባሏት ሩሲያ ላይ አተኩረዋል፤ “ሩሲያ በዩክሬን ላይ እያካሄደችው ባለው አረመኒያዊ ጦርነት ምክኒያት ለዓለም ስራት ዋና የስጋት ምንጫ ሁናለች፤ ከቻይና ጋር የፈጠረችው ወዳጅነትም አሣሳቢ ነው በማለት ጃፓን ቀድመው በሩሲያ ላይ ማዕቀብ ከጣሉት አገሮች ውስጥ በመሆኗ አመስግነዋል። 
ወይዘሮ ቮንዴርል ሌየን አክለውም”፤ “ልክ እንደአውሮፓ ህብረት፤ ጃፓንም፤ አሁን ፈተና ላይ የወደቀው፤ የዩክሬን የወደፊት ሁኒታ፤ ወይም የአውሮጳ የወደፊቲ ሁኔታ ብቻ ሳይሆን በአጣቃላይ የወደፊቱ ያለም ስራት መሆኑን ተረድታለች” በማለት ይህ የጋራ መግባባት ትብብራቸውን እንዲያጠናክሩ እንዳደርጋቸው ገልጸዋል።

 
የጃፓን ጠቅላይ ሚስተር ኩሺዳ  በበኩላቸው፤ ሩሲያ በዩክሬን ላይ የፈጸመችው ወረራ አሳስቢነቱ በአውሮፓ ብቻ ሳይሆን፤ እስያን ጨምሮ ያለማቀፉን ስራት ያናጋ  ነው በማለት ይህን ማንም ሊታገስ እንደማይችልና መቆምም እንዳለበት ማሳሰባቸው ተገልጿል። ሁለቱ ወገኖች በጉባያቸው ማጠቃለያ ባወጡት የጋር መግለጫም፤ ሩሲያ ነጻና ሉላዊት አገር በሆነችው ዩክሬን ላይ የፈጸመችው ህገወጥ ወረራ፤ የዓለማቀፍ ህግንና የመንግስታቱ ድርጅትን መርሆዎች የሚጥስ፤ የአውሮፓንና የአለምን ሰላምም አደጋ ላይ የሚጥል ነው በማለት አጥብቀው ኮንነውታል። ሩሲያ በዩኪረን ላይ ጦርነት ከከፍተች ወዲህ፤ የአውሮፓ ህብረት ሞስኮን ከማውገዝና የማዕቀብ እርምጃዎችን ከመውሰድ ባለፈ’ ሩሲያ ከአለማቀፉ ህብረተብ እንድተገለል ለማድረግም ጥረት  ሲያደረግ የቆየ ሲሆን፤ ለተመሳሳይ ተለዕኮም ካንድ ሳምንት በፊት ወይዘሮ ቮንዴር ሌየን በህንድ ጉብኝት ማድረጋቸው ታውቋል። 
ገበያው ንጉሴ 
ለዲደብሊው 
ብራስልስ 
 

EU - Japan Gipfel
ምስል Dursun Aydemir/AA/picture alliance