1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የአዉሮጳ ከአትላንቲክ ባሻገር ግንኙነት

ሰኞ፣ ጥር 17 2013

የዓለም መንግሥታት የዩናይትድ ስቴትስ 46ተኛ  ፕሬዝዳንት ሆነዉ ለተሾሙት ለዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን የእንኳን ደስ አልዎት የመልካም ምኞት መግለጫን እያስተላለፉ ይገኛሉ።

https://p.dw.com/p/3oOTf
Belgien Brüssel | Pressekonferenz Ursula von der Leyen und Charles Michel
ምስል Thierry Monasse/AA/picture alliance

የአዉሮጳ ሁለቱን አህጉሮች ለማደስ ከምንጊዜዉም በላይ ዝግጁ ነዉ

የአዉሮጳ ሃገራት መንግስታት ከአትላንቲክ ባሻገር ተለሳልሶ የነበረዉ ግንኙነት በአፋጣኝ አጠናክሮ እንዲቀጥል እንደሚፈልጉ እየገለፁም ነዉ። የአውሮጳ ኅብረት የአሜሪካንን እና የአዉሮጳ ኅብረት ግንኙነትን ማደሻው ጊዜ አሁን ነው ሲል ገልፆአል። የኅብረቱ ኮሚሽን ፕሬዝዳንት ኡርዙላ ፎን ዴር ላየ በበኩላቸዉ ሁለቱ አህጉሮች ግንኙነታቸዉን ለማደስ የአዉሮጳ ኅብረት ከምንጊዜዉም በላይ ዝግጁ ነዉ ብለዋል። ይሁንና በአሁኑ ወቅት በአዉሮጳ ኅብረት ሃገራት የኮሮና ወረርሽኝ ስርጭት በመስፋፋቱ ምክንያት ዩናይትድ ስቴትስ ድንበርዋን ዳግም አጥብቃ መዝጋትዋ ተነግሮአል። የሁለቱ አህጉራት ግንኙነት ዳግም በኮሮና ስርጭት ምክንያት ይቀዛቀዝ ይሆን? አዲስ ተመራጩ የአሜሪካ ፕሬዚዳንትስ መቼ ይሆን የአዉሮጳ ጉብኝታቸዉን የሚጀምሩትን ? ከቀድሞዉ ፕሬዚዳንት ትራምፕ በኋላ የአዉሮጳ እና የአሜሪካ ግንኙነት ምን ይጠብቀዉ ይሆን? የእለቱ ማኅደረ ዜና የሚዳስሰዉ ርዕስ ነዉ። 

 

አዜብ ታደሰ

ኂሩት መለሰ