የአዉሮጳ ኅብረት ለአባላቱ ድጋፍ እሰጣለሁ አለ
ረቡዕ፣ መጋቢት 9 2012ማስታወቂያ
የኮረና ተዋሕሲ ክፉኛ እየተሰራጨበት ባለበት አውሮጳ፤ የሕብረቱ አባል ሃገራት የተዋህሲውን ስርጭት ለመግታት ከሚወስዷቸው የጥንቃቄ እርምጃዎች ጎን ለጎን ህብረቱ የከፋ የኢኮኖሚ ጉዳት ለሚያጋጥማቸው አባል ሃገራቱ ድጋፍ ለማድረግ ዝግጁ መሆኑን አስታውቋል። ተዋህሲው ክፉና የተሰራጨባቸው አብዛኞቹ አባል ሃገራት ድንበሮቻቸውን ከመዝጋት ባሻገር ዜጎቻቸው ከቤት እንዳይወጡ የሚያስገድዱ ክልከላዎችን መጣል ጀምረዋል።
ገበያው ንጉሴ
ታምራት ዲንሳ