የአዉሮጳ መሪዎች ጉባኤ ተሰረዘ
ዓርብ፣ መስከረም 15 2013ማስታወቂያ
የአዉሮጳ ሕብረት አባል ሐገራት መሪዎች ትናንትና ዛሬ ሊያደርጉት የነበረዉ ጉባኤ ተሰረዘ። ጉባኤዉ የተሰረዘዉ የሕብረቱ ምክር ቤት ፕሬዝደንት ሻርልስ ሚሼል በኮሮና ተሕዋሲ ተይዘዋል በሚል ጥርጣሬ ዉሽባ በመግባታቸዉ ነዉ። መሪዎቹ በግሪክና ቱርክ ጠብ፣ በቤሎሩስ ፖለቲካዊ ቀዉስንና በስደተኞች ጉዳይ ላይ ተነጋግረዉ ይወስናሉ ተብሎ ነበር። ጉባኤዉ በመጪዉ ሳምንት ይደረጋል ተብሎ ይጠበቃል።
ገበያዉ ንጉሤ
ነጋሽ መሐመድ
እሸቴ በቀለ