1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የአዉሮጳ መሪዎች የሁለት ቀን ስብሰባና ዉጤቱ

ዓርብ፣ ጥቅምት 6 2013

ለሁለት ቀናት ብረስልስ ላይ የተካሄደዉ የአዉሮጳ ኅብረት ሃገራት የመሪዎች ጉባዔ አጣዳፊና ወሳኝ ባላቸዉ ርዕሶች ላይ ተወያይቶ ዉሳኔዎችን አሳልፎአል። አዉሮጳ  ለሁለተኛ ጊዜ ባገረሸዉ የኮሮና ወረርሽኝ እየተናጠ  ባለበት በአሁኑ ወቅት የሃገራቱ መሪዎችም የኮሮና ተኅዋሲ ስርጭት ለመግታት በሚያስችል ነጥቦች ላይ ተወያይተዋል።

https://p.dw.com/p/3k24d
Belgien EU-Gipfel Impfstrategie | Stella Kyriakides und Margaritis Schinas
ምስል Olivier Hoslet/Reuters

የኮሮና ወረርሽኝ፤ ብሪታንያ ከኅብረቱ መዉጣት፤እና የከባቢ አየርን መጠበቅ ላይ ተወያይተዋል

 

ለሁለት ቀናት ብረስልስ ላይ የተካሄደዉ የአዉሮጳ ኅብረት ሃገራት የመሪዎች ጉባዔ አጣዳፊና ወሳኝ ባላቸዉ ርዕሶች ላይ ተወያይቶ ዉሳኔዎችን አሳልፎአል። አዉሮጳ  ለሁለተኛ ጊዜ ባገረሸዉ የኮሮና ወረርሽኝ እየተናጠ  ባለበት በአሁኑ ወቅት የሃገራቱ መሪዎችም የኮሮና ተኅዋሲ ስርጭት ለመግታት እና ወረርሽኙ የሚያደርሰዉን የጤና ማኅበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ተጽኖ ለመቋቋም በግል እና በጋራ ሊወሰዱ በሚገባቸዉ እርምጃዎች ላይ አተኩረዋል። ብሪታንያ ከኅብረቱ በምትወጣበት ሁኔታ በተደረሰዉ ስምምነት መሰረት በሚቀጥለዉ የጥር ወር የሽግግር ጊዜዋን ጨርሳ የምትሰናበት ጊዜ ሲሆን በብሪታንያ እና በአዉሮጳ ኅብረት ቀጣይ ግንኙነት እና የንግድ ስምምነት ላይ ግን እስካሁን በመግባብያ ነጥብ ላይ ባለመደረሱ የኅብረቱ መሪዎች በዚህም ላይ ትኩረት ሰጥተዉ ተወያይተዋል። ከዚህ ሌላ መሪዎቹ በአየር ለዉጥ እና በዉጭ ግንኙነቶች በተለይም ኅብረቱ ከአፍሪቃ ጋር ስለሚኖረዉ ሁለንተናዊ ግንኙነት እና ቱርክ እና ሩስያም ከኅብረቱ ጋር ስለገቡባቸዉ ዉዝግቦች መሪዎቹ ዉሳኔዎቹን አሳልፈዋል።    

ገበያዉ ንጉሴ

 

አዜብ ታደሰ

ሸዋዬ ለገሠ