1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የአዉሮጳ ሕብረት ጦርና ሊቢያ

ረቡዕ፣ መጋቢት 30 2012

ጠቅላይ ዕዙን ሮም-ኢጣሊያ ያደረገዉ ጦር ወደ ሊቢያ የሚገባ ጦር መሳሪያንና ከሊቢያ በሕገ-ወጥ መንገድ የሚወጣ ነዳጅ ዘይትን ባየር፣በባሕርና በሳተላይት እየተከታተለ ይይዛል።የሊቢያ ተፋላሚ ኃይላትና ደጋፊዎቻቸዉ መንግስታት ሐብታሚቱን ሐገር የሚያወድመዉን ጦርነት ለማቆም በተደጋጋሚ ቃል ቢገቡም እስካሁን ቃላቸዉን አላከበሩም

https://p.dw.com/p/3aehR
Libyen - Mission "Irini" soll Waffenembargo gegen Libyen überwachen
ምስል picture-alliance/dap/BMVg/Bundesverteidigungsministerium

የአዉሮጳ ሕብረት ባሕር ጦር ዘመቻ

የአዉሮጳ ሕብረት በሊቢያ ላይ የተጣለዉን ዓለም አቀፍ የጦር መሳሪያ ሽያጭ ዕገዳ እንዲቆጣጠር ያዘመተዉ የባሕር ኃይል ጦር ካለፈዉ ሳምንት ጀምሮ ምስራቃዊ ሜድትራኒያን ባሕር ላይ ሠፍሯል።ጠቅላይ ዕዙን ሮም-ኢጣሊያ ያደረገዉ ጦር ወደ ሊቢያ የሚገባ ጦር መሳሪያንና ከሊቢያ በሕገ-ወጥ መንገድ የሚወጣ ነዳጅ ዘይትን ባየር፣በባሕርና በሳተላይት እየተከታተለ ይይዛል።የሊቢያ ተፋላሚ ኃይላትና ደጋፊዎቻቸዉ መንግስታት ሐብታሚቱን ሐገር የሚያወድመዉን ጦርነት ለማቆም በተደጋጋሚ ቃል ቢገቡም እስካሁን ቃላቸዉን አላከበሩም።ዓለም ሙሉ ትኩረቱን የኮረና ተሕዋሲን ስርጭት በመከላከሉ ላይ ባደረገበት ባሁኑ ወቅት፣ የሊቢያ ተፋላሚ ኃይላትና አስታጣቂዎቻቸዉ ዉጊያዉን ያባብሱታል የሚል ስጋት አለ።

ገበያዉ ንጉሴ 

ነጋሽ መሐመድ

አዜብ ታደሰ